ቀጥታ፡

በጣሊያን የባህር ዳርቻ አካባቢ የስምንት ወር ህፃንን ጨምሮ ስደተኞች መሞታቸው ተገለፀ

መስከረም 27 /2012 በጣሊያን የባህር ጠረፍ ሜዲትራኒያን ባህር ውስጥ ሰጥመው ከነበሩ መካከል የ13 ሴቶችን አካል የጣሊያን የባህር ጠባቂዎች ማውጣታቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን አፍሪካ በድረ ገጹ አስነብቧል። ለስደተኞቹ ሞት በከፍተኛ አየር ጠባይ ለውጥ የተሳፈሩባት ጀልባ በደቡባዊ የሲሲሊ ደሴት ላምፔዱሳ ጠረፍ  አካባቢ መስመጧን ተከትሎ እንደሆነ የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ከተረፉት አንዷ ለሲ ጂ ቴኤን እንደተናገረችው በአደጋው  እህቷንና  ሌላ የስምንት ወር  የእህቷን ልጅ እንዳጣች በሃዘን በተሰበር ልብ ተናግራለች፡፡ የባህር ዳርቻ ጠባቂዎች እንዳስታወቁትም ከመስመጥ የተረፍ 22 ሰዎችን የታደጉ ቢሆንም በርካታ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረም ገልፀዋል፡፡ በሜዲትራኒያን ባህር በኩል ወደ አውሮፓ ለመድረስ የሚደረገው ጥረት እጅግ አስቸጋሪውና ረጅሙ መስመር እንደሆነም መረጃው አስፍሯል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ እንዳስታወቀው ከሆነም መነሻዋን ከቱኒዚያ ያደረገችው ጀልባ 50 ሰዎችን ጭና ጉዞ የጀመረች ሲሆን አብዛኞቹ ስደተኞችም ከቱኒዚያና ከምዕራብ አፍሪካ የመጡ ናቸው ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም