ቀጥታ፡

ጃፓን በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ ትደግፋለች - --አምባሳደር ዳይሱኬ ማትሱንጋ

መስከረም 27/2012 ጃፓን በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ እንደምትደግፍ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ዳይሱኬ ማትሱንጋ ተናገሩ። አምባሳደሩ በተለይም ለኢዜአ እንደገለጹት ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በግሉ ዘርፉ መነቃቃት እንዲፈጠር እርምጃ መውሰዳቸውን አንስተዋል። በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ኢትዮጵያ የካይዘን ፍልስፍናን መተግበሯን አስታውሰው፤ ይህም የቀላል ኢንዱስትሪዎች ምርት እንዲሻሻልና የኤክስፖርት መጠን እንዲጨምር አዎንታዊ ሚና እንደነበረው ተናግረዋል። የወቅቱ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አንዱ ትኩረት የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ በመሆኑ የጃፓን ኩባንያዎች በቴክኖሎጂ መስኮች በመሰማራት የስራ ዕድል አማራጮችን ለመፍጠር ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። ጃፓን የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ሪፎርም እንደምትደግፍ የገለጹት አምባሳደሩ፤ በትምህርት፣ በስራ ዕድል ፈጠራና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗንም አረጋግጠዋል። ከኢትዮጵያ ባለፈ እንደ ኤርትራ ካሉ ጎረቤት አገራት ጋር ከኢኮኖሚ ግንኙነት በተጨማሪ በሠላምና መረጋጋት ላይ በትብብር እንደምትሰራም ተናግረዋል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም