አምባሳደር ሀሰን ታጁ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሴኔጋል ፕሬዝዳንት አቀረቡ - ኢዜአ አማርኛ
አምባሳደር ሀሰን ታጁ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሴኔጋል ፕሬዝዳንት አቀረቡ

አዲስ አበባ መስከረም 27 /2012 በሴኔጋ የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሀሰን ታጁ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚቴስትር አስታወቀ። አምባሳደር ሀሰን የሹመት ደብዳቤያቸውን ያቀረቡት ከትናንት በስትያ መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው። ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል በዚሁ ወቅትም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ እንደሚያደንቁ ገልጸዋል። አምባሳደሩ በቆይታቸው የሃገራቸው ህዝብ እና መንግስት ድጋፍ እንደማይለያቸውም ፕሬዚዳንቱ አረጋግጠውላቸዋል። ኢትዮጵያ እና ሴኔጋል ኤምባሲዎቻቸውን በአገራቱ ዋና ከተሞች በመክፈት ከግማሽ ምዕተ አመት በላይ ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው።