የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ለኢሬቻ በዓል መከበር ህዝቡ ላደረገው ቀና ትብብር ምስጋና አቀረበ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ለኢሬቻ በዓል መከበር ህዝቡ ላደረገው ቀና ትብብር ምስጋና አቀረበ
ኢዜአ፤መስከረም 25/2012 የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲከበር ህዝቡ ላደረገው ቀና ትብብርና ድጋፍ ምስጋናውን አቅርቧል። የኢሬቻ ክብረ በዓል መስከረም 24 እና 25 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማና በቢሾፍቱ መከበሩ ይታወሳል።
ለዚህ ክብረ በዓል በሰላም መከበር ህዝቡ ላደረገው ቀና ትብብርና ድጋፍ ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል።
በፀጥታ ጥበቃው ላይ የተሰማሩት የሰራዊቱ አባላት የተሰጣቸውን አገራዊ ተልዕኮ በብቃት በመወጣት የታለመውን ግብ ማሳካታቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል።
"ለዚህ ስኬት ትልቁን ድርሻ የተወጣችሁ አባገዳዎች፣ ወጣቶች እና የበዓሉ ታዳሚዎች ለፀጥታ አስከባሪ አካላት ያሳያችሁት ቀና ትብብር አርአያነት ያለው ተግባር ነው" ብሏል።
''ህዝብና ፖሊስ አብሮ ተባብሮ ከሰራ የማንሻገረው የሰላምና የደህንነት ችግር አለመኖሩን አረጋግጠናል'' በማለት፤ የኢትየጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምስጋናውን ገልጿል።