የኢሬቻ በዓል በካርቱምና ፖርት ሱዳን ተከብሯል - ኢዜአ አማርኛ
የኢሬቻ በዓል በካርቱምና ፖርት ሱዳን ተከብሯል
ኢዜአ፤ መስከረም 24/2012 በሱዳን ካርቱምና ፖርት ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት የኢሬቻ በዓል ተከብሯል ። በዓሉ በካርቱም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ሱዳናውያንና ሌሎች የክብር እንግዶችና በተገኙበት ነው የተከበረው። በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ፤ ኢሬቻ የኦሮሞ ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያዊያን በዓል ነው ብለዋል። በተጨማሪም በዓሉ በፖርት ሱዳን የሚገኙ ማህበረሰቦችና በቀይ ባህር አካባቢ በኦዶሎታ ስዋኪን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ተከብሯል። 
በካርቱም በተከበረው የእሬቻ በዓል ላይ የውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ መገኘታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።

በካርቱም በተከበረው የእሬቻ በዓል ላይ የውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ መገኘታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።