የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሽን ጽህፈት ቤት በኢንስፔክሽን ዘርፍ ዓለም ዓቀፍ እውቅና አገኘ

67
አዲስ አበባ መስከረም 23/2012  የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሽን ጽህፈት ቤት በኢንስፔክሽን አክሬዲቴሽን አይኤስኦ/አይኢሲ 17020 /2012 ዓለም ዓቀፍ እውቅና ማግኘቱን ገለፀ፡፡ ይህ እውቅና በህክምና ላቦራቶሪ አይ ኤስ ኦ (ISO) 15189፡2012 እና የፍተሻ ላቦራቶሪ አይ ኤስ ኦ/አይ ኢ ሲ 170252017 ካገኘው ዓለም አቀፍ እውቅና በተጨማሪ የተገኘ ነው። በመሆኑም በኢንስፔክሽን አክሬዲቴሽን አይ ኤስ ኦ/አይ ኢ ሲ 17020 /2012 ዓለም ዓቀፍ እውቅና ማግኘቱን ፅህፈት ቤቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ አመልክቷል። ያገኘውን ዓለም ዓቀፍ እውቅና በማስጠበቅ በሰርቲፍኬሽንና በካሊብሬሽን ዘርፎች የዓለም ዓቀፍ እውቅና ለማግኘት እየሰራ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡ በኢንስፔክሽን ዘርፍ ዓለም ዓቀፍ እውቅና ለማግኘት በአፍሪካ አክሬዲቴሽንና በዓለም አቀፍ የላቦራቶሪ አክሬዲቴሽን ትብብር ከግንቦት 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በተከታታይ ለአምስት ቀናት ግምገማ ተደርጎበት ነበር፡፡ በግምገማው የተገኙ ክፍተቶችን አስተካክሎ ለገምጋሚ ቡድኑ በማቅረቡ በኢንስፔክሽን አይኤስኦ/አይኢሲ 17020 / 2012 ዘርፉ ዓለም ዓቀፍ እውቅና ማግኘት ችሏል፡፡ ዘርፉ ዓለም ዓቀፍ እውቅና ማግኘቱ በተለይ ሃገሪቱ ወደ ውጭ የምትልካቸው ጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎችና ሌሎች ምርቶች የኢንስፔክሽን ሥራ እየሰሩ ሰርተፍኬት ለሚሰጡ ተቋማት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለውም መግለጫው ጠቅሷል፡፡    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም