ቀጥታ፡

የበዓሉ ታዳሚዎች እሬቻ ከሚፈቅዳቸው ስነ ስርዓቶች ውጪ ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሊቆጠቡ ይገባል--- የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን

ኢዜአ፤ መስከረም 22/2012 የእሬቻ በዓል ታዳሚዎች በዓሉ ከሚፈቅዳቸው ስነ ስርዓቶች ውጪ ግጭት ከሚቀሰቅሱ እንቅስቃሴዎች ሊቆጠቡ እንደሚገባ  የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አሳሰበ፡፡ ኮሚሽኑ ለእሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት በማስተላለፍ በአዲስ አበባ እና በቢሾፍቱ ለሚከበረው የእሬቻ በዓል ያደረገውን ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል። የተለያዩ አካላት የእሬቻን በዓል ለማደናቀፍ፣  የራሳቸውን አጀንዳ ለመፈጸም እና ለጥፋት ሊጠቀሙባቸው የነበሩ የጦር መሳሪያዎችና ቦንምቦች ወደ አዲስ አበባ ሊገቡ ሲሉ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ኮሚሽኑ  በመግለጫው አስታውቋል። የጦር መሳሪያዎቹን ለማስገባት ሲሞክሩ የነበሩ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተጠቅሷል፡፡ የበዓሉ ታዳሚዎች የእሬቻ በዓል ከሚፈቅዳቸው ስነ ስርዓቶች ውጪ ግጭት የሚቀሰቅሱ ልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎችን ከማድረግ እንዲሁም የማህበረሰቡን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ድርጊቶችን ከመፈፀም እንዲቆጠቡም አሳስቧል።   ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ ከሀገራችን አልፎበዓለም ከማይዳሰሱቅርሶች አንዱ ሆኖ በዩኒስኮ የተመዘገበው ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ በርካታ የውጭ ጎብኝዎች የታደሙበት የመስቀል ደመራ ክብረ በዓል በአዲ ስአበባ ከተማና በመላው ሀገራችን በድምቀትና በሰላም መከበሩይ ታወሳል። ለዚህም በዓል በሰላም መከበር መላው የሀገራችን  ህዝቦች ላደረጋችሁት ቀና ትብብርና ድጋፍ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ላቅ ያለ ምስጋናውን ማቅረብ ይወዳል። እንደ ደመራ በዓል ሁሉ ከዘመን መለወጫ በዓል ጋርተያይዞ ሌላው በየአመቱ በአደባባይ በድምቀት ከሚከበሩ የማይዳሰሱ የሀገራችን ቅርሶችውስጥ የሰላምና የአንድነት ተምሳሌት የሆነው የኢሬቻ በዓል አንዱ ነው፡፡ በዚሁ የሀገራችን ባህላዊ የእምነት እሴት መገለጫ በሆነው የኢሬቻ ክብረ በዓል ላይ ከኦሮሞ ህዝብ ባሻገር መላው የሃገራችን ህዝቦችና የውጭ ሀገር ጎብኝዎች የሚሳተፉበት ታላቅ በዓል ነው፡፡ ዘንድሮ በአዲስ አበባ ከተማ መስከረም 24 ቀን እና በቢሾፍቱ ከተማ መስከረም 25 ቀን 2012 ዓ/ም በድምቀት የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል ለማደናቀፍ፣ የተለያዩ አካላት የራሳቸው አጀንዳ ለማስፈፀም እናለጥፋት ይጠቀሙበት የነበሩ የጦር መሳሪያዎችና ቦንቦችን ወደ አዲስ አበባ ከተማ ለማስገባት ሲሞክሩ ከዘጠኝ ተጠርጣሪዎች ጋር በህብረተሰቡ ትብብርና በፀጥታ ሀይሉ የተቀናጀ ጥረት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮሚሽኑ ማስገንዘብ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መላው የሀገራችን ህዝቦች፤ በተለይም ደግሞ የበዓሉ ታዳሚዎች የኢሬቻ በዓል ከሚፈቅዳቸውስነ-ስርዓቶች ውጪ ግጭት የሚቀሰቅሱ ልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ፣ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ስለሆነ አባገዳዎች፣ የኢሬቻ በዓል አዘጋጅ ኮሚቴዎች፣ይህንን በዓል በደመቀ ሁኔታና በሰላም እንዲከበር የምታስተባብሩ ፎሌዎች፣ቄሮዎች፣በጎፍቃደኛ ወጣቶች፣በተለይም ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና የወጣቶችፌዴሬሽን፤ፖሊስ የሚሰጠውን መመሪያ ከግምት ውስጥ በማስገባት በዓሉ በሰላም ተጀምሮ እንዲያልቅ አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ እንድታደርጉ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስኮ ሚሽን በአክብሮት ይጠይቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የበዓሉ ተሳታፊዎች በዓሉን ስታከብሩ የተለየ እንቅስቃሴ ስትመለከቱ በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት የተለመደ ትብብራችሁን እንድታደርጉ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ በዚህ አጋጣሚ የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባና በቢሾፍቱ ከተማ ያለምንም የፀጥታ ስጋት በሰላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ያደረጉ መሆኑን እየገለፅን በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የደስታ እንዲሆንልን የኢትዮጵ ያፌዴራል ፖሊስኮሚሽን ይመኛል፡፡ መልካም በዓል!  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም