ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የማሊ ወታደሮች ተገደሉ - ኢዜአ አማርኛ
ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የማሊ ወታደሮች ተገደሉ
ኢዜአ መስከረም 21/2012ተጠርጣሪ ጂሃዲስቶች ቦርኪና ፋሶ ድንበር አቅራቢያ ባሉ ሁለት ወታደራዊ ጣቢያዎች ባደረሱት ጥቃት 25 ወታደሮች ሲገደሉ 60 ያህሉ የደረሱበት አለመታወቁን የማሊ መንግስት አስታወቀ፡፡ ከበድ ያለ ውጊያ መቀጠሉን ያወሳው የቢቢሲ ዘገባ የማሊ መንግሰት በጥቃቱ የጦር መሳሪያዎች ጭምር ማጣቱን አውስቷል፡፡
የማሊ ጦር ለጥቃቱ በሰጠው ምላሽ በአየር ጭምር በመታገዝ ጦርነቱን ሲያካሂድ ከቦርኪና ፋሶ ሃይልም እገዛ አግኝቷል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2012 ጀምሮ በማሊ ውስጥ የጃሂዲስት አመፅ እና የጎሳ አቀንቃኞች በማሊ ግጭት እንዲፈጠር ምክንያት እንደሆኑም በመረጃው ተጠቅሷል ፡፡ ማሊ በሳሃል ቀጠና በፀረ-ሽብርተኝነት ላይ ከሚሰሩ ኃይሎች አባል ሀገር ስትሆን አባል ሃገራቱም ቡርኪና ፋሶ፣ ቻድ ፣ ኒጀር እና ሞሪታኒያ ናቸው ፡፡ ጂ-5 ሳሃል ተብሎ የሚጠራው በ3ሺ ጠንካራ የፈረንሣይ ኃይል የታገዘ እንደሆነም በመረጃው ሰፍሯል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በቀጠናው ብጥብጥ እየተባባሰ መሄዱ እንዳሳሰባቸው መግለፃቸውን ዘገባው አስፍሯል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2012 እስከ 2018 ድረስ የንፁሃን ዜጎች ሞት በአራት እጥፍ መጨመሩንም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡