የሩስያ የልዑካን ቡድን አባላት ዛሬ በጎንደር ከተማ ጉብኝት ያደርጋሉ - ኢዜአ አማርኛ
የሩስያ የልዑካን ቡድን አባላት ዛሬ በጎንደር ከተማ ጉብኝት ያደርጋሉ
ጎንደር (ኢዜእ) መስከረም 19/ 2012 የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክስርቲያን የውጪ ጉዳይ ኃላፊዎችና የሩሲያ የሚዲያ አባላት በዛሬው እለት በጎንደር ከተማ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገለጸ፡፡ የጎንደር ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያኖች ሕብረት ጸሐፊ አቶ ብርሃኑ አያሌው ለኢዜአ እንደተናገሩት ዘጠኝ አባላት ያሉት የልኡካን ቡድኑ በጎንደር ከተማ የሁለት ቀናት ጉብኝት ያካሂዳል፡፡ የልኡካን ቡድኑ አባላት በቆይታቸው የአብነት ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በኢትዮጵያ ብቸኛ የሆነውን “የባታ ደብረ ኃይል ወደብረ ጥበብ ባህታ ለማሪያም ካቴድራል የአቋቋም ትምህርት ቤትን” ይጎበኛሉ፡፡ በጎንደር ከተማ የሚገኙ የመንበረ መድኃኒዓለም፣ የቁስቋምና የደብረ ብርሃን ስላሴ ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናትን የሚጎበኙ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የልዑክ ብድኑ አባላት በዓለም ቅርስነት የተመዘገበውን የፋሲል ቤተ-መንግስት እንደሚጎበኙ ይጠበቃል ፡፡