ቀጥታ፡

ኢትዮጵየዊያን ሴት የማራቶን ሯጮች ውድድሩን አቋረጡ

መስከረም  17/2012 በኳታር ዶሃ እየተካሄደ ባለው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች ማራቶን ውድድር የተሳተፉ ኢትዮጵየዊያን አትሌቶች ውድደሩን አቋርጠው ወጡ። በአጠቃላይ የዶሃ አየር ሙቀት የከበዳቸው 28 አትሌቶች የማራቶን ውድድሩን አቋርጠዋል። በ17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና  በሴቶች ማራቶን ኢትዮጵያንየወከሉት አትሌት ሮዛ ደረጀ፣ አትሌት ሩታ ኣጋ እና አትሌት ሹሬ ደምሴ ናቸው። ይሁን እንጂ  ሁሉም አትሌቶች ውድድሩን ሳያጠናቅቁ አቋርጠው ወጥተዋል። ኬኒያዊቷ ሩት ኬፔንጌቲች የዘንድሮው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮ ሴቶች ማራቶን አሸናፊ ሆናለች። አትሌቷ ውድድሩን ያጠናቀቀችው በ2 ሰዓት፣ 32 ደቂቃ 43 ሰከን ጊዜ ውስጥ ነው። የባህሬን ዜግነት ያላት ሮዝ ጭሊሞ ሁለተኛ፤ የናሚቢያዋሄላሊያ ጆሃንስ ደግሞ ሶሰተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል። ትናንት በተካሄደው በዚሁ ውድድርከተሳተፉት 68 ሴት አትሌቶች መካከል ውድድሩን ማጠናቀቅ የቻሉት 40 ብቻ ናቸው። አትሌቶቹ ውድድሩን ያቋረጡት በዶሃ ያለውን ከፍተኛ ሙቀት መቋቋም ተስኗቸው መሆኑም ተገልጿል። የሙቀቱን ጫና መቀነስ እንዲቻል ውድድሩ በምሽት እንዲካሄድ የተደረገ ቢሆንም ሙቀቱ ከ30 ዲግሪ መቀነስ አልቻለም፤ በእርጥበት ምክንያት የመተመዘገበው ወበቅ ደግሞ ከ80 በመቶ ሊወርድ እንዳልቻለ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በዚህም የተነሳ 28 የውድድሩ ተሳታፊዎች ውድድሩን ለማቋረጥ ተገደዋል። ውድድሩን በአንደኝነት ያጠናቀቀችው ኬንያዊቷ ሩት ኬፔንጌቲችም ብትሆን ጋዜጠኞች እያነጋገሯት ሳለች ተዝለፍልፋ ወድቃለች። የገባችበት ጊዜም በርቀቱ ቀደም ሲል ከተያዘው በእጅጉ ያነሰ፤ ከግል ሰዓቷም በ15 ደቂቃ ዝቅ ያለ መሆኑም ተመልክቷል። በሌላ በኩልኢትዮጵያን የተካፈሉበት የ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ማጣሪያ ውድድር ትናንት የተካሄደ ሲሆን ጥላሁን ሀይሌ፣ ሰለሞን ባረጋና ሙክታር እንዲሪስ ማጣሪያውን  አልፈዋል፤ አባዲ ሀዲስ ግን ከውድድሩ ውጭ ሆኗል። እንዲሁም በሴቶችየ3 ሺህ መሰናክል ማጣሪያ አትሌት መቅደስ አበበ ብቻ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። አትሌት ሎሚ ሙለታና አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ  ግን ሳይሳካላቸው ቀርቷል። በሴቶች 800 ሜትር ኢትዮጵያን የወከለችው ድርቤ ወልተጂ የመጀመሪያውን ማጣሪያውን ማጣሪያ አልፋለች። በኳታር አስተናጋጅነት ዶሃ ላይ ትናንት የተጀመረው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን ውድድር ለመጪዎቹ ስምንት ቀናት ይካሄዳል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም