በትራፊክ አደጋ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ

መስከረም  17/2012 በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ዛሬ ሌሊት በተከሰተ የተሽከርካሪ አደጋ የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ኢንስፔክተር መሃመድ አሊ ለኢዜአ እንደገለጹት ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በደረሰው የትራፊክ አደጋ ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ በ14 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል። ከሟቾቹ መካከል የደብረብርሃን ከተማ ትራፊክ ፖሊስ አባልን ጨምሮ ሦስት የአንድ ሰው ቤተሰቦችና ሁለት ህጻናት እንደሚገኙበት ኢንስፔክተር መሃመድ አስታውቀዋል። ጉዳት የደረባቸውን ሰዎች ወደ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታና አጣዬ የመጀመ ደረጃ ሆስታል በማጓጓዝ ህክምና እንዲያገኙ እየተደረገ ነው ተብሏል። አደጋው የደረሰው 24 ሰዎችን አሳፍሮ ከአዲስ አባ ወደ ደሴ ሲጓዝ የነበር ኮድ3- ኤ71430 አአ ሀይሩፍ ከተቃራኒ አቅጫ ይጓዝ ከነበረ ኢት- ኮድ 3- 91889 ከሆነ ተሳቢ መኪና ጋር በመጋጨቱ መሆኑ ተመልክቷል። የተሳቢዉ አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን የሀይሩፉ አሽከርካሪ በህይወት መኖሩ አለመኖሩን ለማረጋገጥ የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል። የአደጋው መንስኤም መንገዱ ጠመዝዛ ከመሆኑ አንጻር ከፍጥነት በላይ በማሽከርከር ሳይሆን እንደማይቀር አስታውቃል። የሌሊት ጉዞ ህገ ወጥ መሆኑን በተደጋጋሚ ቢገለጸም አሽከርካሪዎችም ሆኑ ህብረተሰቡ ከእንደዚህ ዓይነት ህገ ወጥ ድርጊት በመቆጠብ ህይወትንና ንብረትን ለማዳን የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም