ቀጥታ፡

እንግዶች የደመራን በዓል ለማክበር መስቀል አደባባይ እየደረሱ ነው

መስከረም 16/2012 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ አቡነ ማቲያስ እና የቤተክርስቲያኗ 4ኛው ፓትሪያርክ ብጹዕ አቡነ መርቆሪዮስ መስቀል አደባባይ ደርሰዋል። የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳውም በዓሉን ለመታደም በስፍራው የተገኙ ሲሆን በመዲናዋ የሚገኙ የውጭ አገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶችም በመስቀል አደባባይ የተዘጋጀላቸውን ስፍራ እየያዙ ነው። የበዓሉ አከባበር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ አቡነ ማቲያስ ፀሎተ ቡራኬ የሚጀመር ሲሆን የተለያዩ ሃይማኖታዊ ዝግጅቶች ይከወናሉ፤ በመጨረሻም ደመራ ይለኮሳል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም