ቀጥታ፡

የአየር ብክለት ተከራካሪዋ ግሪታ ቱነበርግ የስዊድን የኦልተርኔቲቭ ኖብል ሽልማት አሸናፊ ሆነች

ኢዜአ፤ መስከረም 14/2012 ታዳጊዋ የአየር ንብረት ተሟጋች ግሪታ ቱነበርግ የስዊድን የኦልተርኔቲቭ ኖብል ሽልማት አሸናፊ መሆኗን የስዊድን የሰብአዊ መብት ሽልማት ድርጅት አስታውቋል፡፡

የስነፍጥረት መብት ፋውንዴሽን በመግለጫው እንዳስታወቀው ቱነበርግ ለሽልማት የበቃችው የአየር ንብረት መዛባትን ለመከላከል ባካሄደችው ዘመቻ ነው፡፡

ቱነበርግ ሳይንሳዊ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ በአየር ብክለት የሚደርሰውን ጉዳት በማስተጋባቷ በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ መነቃቃት እንዲፈጠር ማድረጓንም አመላክቷል፡፡

የ16 አመቷ ታዳጊ እያካሄደች ያለው ዘመቻ እየተባባሳ በመጣው የአየር ንብረት መዛባት አስመልካታ ባደረገችው ቅስቀሳ በሚሊዮኖች ዘንድ መነቃቃት በመፍጠሩ ለጉዳዩ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሠጥ ድምፃቻውን እያሰሙ መሆናቸውንም ፋውንዴሽኑ አመላክቷል፡፡

የቱነበርግ አለም አቀፍ አየር ንብረት ዘመቻ እኤአ በነሀሴ በ2018 በሲዊድን ፓርላማ ፊትለፊት ከደጋፊዎቿ ጋር የተቃውሞ ድምጽ በማሰማት መጀመሩን ኤኤፍፒ በዘገባው አስታውሷል፡፡

በሽልማቱ 103 ሺ በላይ ዶላር እንደሚበረከትላትም ነው ዘገባው ያመላከተው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም