ቀጥታ፡

ድርጅቱ በኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

ጋምቤላ (ኢዜአ) መስከረም 14 / 2012 የተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት በኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በድርጅቱ የኢትዮጵያ ተጠሪ ሚስ አደል ካሆደር አስታወቁ፡፡ ተጠሪዋ በጋምቤላ ክልል በድርጅቱ ድጋፍ በመከናወን ላይ ባሉት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ዛሬ በጋምቤላ ከተማ ተወያይተዋል፡፡ በድርጅቱ የኢትዮጵያ ተጠሪ ሚስ አደል ካሆደር በውይይቱ መድረኩ ላይ እንዳሉት ሀገሪቱ ለዜጎች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማትን ተደራሽ በማድረግ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረት አድንቀዋል፡፡ መንግስት በተለይም የህጻናትን ደህንነት ለማስጠበቅና የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን መመልከታቸውንም ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም በትምህርትና በጤና ተቋማት ተደራሽነት ፡በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፡ በመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታና ሌሎችም ዘርፎች የሚደረገው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅትም እነዚህን ዘርፎች ውጤታማ ለማድረግና ህብረተሰቡ የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡ በተጨማሪምድርጅቱየሀገሪቱመንግስትለጀመራቸው የሰባዊ ሀብትልማትሥራዎች መጠናከርላይትኩረትአድርጎእንደሚሰራምተናግረዋል፡፡ ድርጅቱ በመላው ሀገሪቱ በበርካታ ዘርፎች የተለያዩ ድጋፎችን እደረገ ነው ያሉት ሚስ አደል ካሆደር ለውጤታማነቱ በየደረጃው የሚገኙ አካላት የሚያደርጉትን ጥረት ማጠናከር እንዳለባቸውም ጠይቀዋል፡፡ በጋምቤላ ክልልም በትምህርት ተደራሽነት፡በጤናና በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እንዲሁም በሌሎችም ዘርፎች የሚደረገውን ድጋፍ እንደሚያጠናክሩም ተናግረዋል፡፡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በበኩላቸው ድርጅቱ በክልሉ በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ዘርፎች እያደረገ ባለው ድጋፍ በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡ በተለይም በትምህርት፣ በጤና፣ በንጽህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና በሌሎችም ዘርፎች ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል። ድርጅቱ በቀጣይ ከክልሉ የኤች አይ ቪ ኤድስን በሽታ ለመግታትና በሌሎችም ዘርፎች በተጀመሩት ስራዎች ላይ ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።              
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም