ሁሉንም ልጆቿን በእኩልነት የምታስተናግድ ኢትዮጵያን ለመፍጠር መስራት አለብን- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

68
አዲስ አበባ  መስከረም 11/2012  "ሁሉንም ልጆቿን በእኩልነት የምታስተናግድ ኢትዮጵያን ለመፍጠር እጅ ለእጅ ተያይዘን በብልሃት መስራት አለብን" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደቡብ ክልል ሃዲያ ዞን በመገኘት ከሆሳዕና ከተማና የአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ይይት አድርገዋል። ቀደምት አባቶችና እናቶች ያቆዩልንን አገር የማስቀጠል ኃላፊነት የአሁኑ ትውልድ ትልቅ ሃላፊነት እንዳለበት የገለጹት ጠቅላይ ሚኒሰትሩ፤ ስለ ልዩነትና ጥላቻ ሳይሆን በጋራ ሰርቶ በጋራ ማደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ይገባል ብለዋል። በርካታ የሃድያ ዞን ወጣቶች ብዙ ገንዘብ በማውጣት ከመሰደድ ይልቅ "በአገሬ ሰርቸ መለወጥ እችላለሁ" የሚል እምነት ይዘው መስራት እንደሚጠበቅባቸው መክረዋል። የዞኑ አስተዳድር ለወጣቶች የስራ እድል ለመፈጠር በሚያደርጋቸው ተግባራትም የፌዴራል መንግስት ድጋፍ እንደሚያደረግ አረጋግጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ሳምንት በደቡብ ክልል ካፋ ዞን ተገኝተው ከቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ህዝባዊ ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል።                  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም