የአባይ ድልድይ ግንባታ ሊጀመር ነው

229
መስከረም 9/2012 በባህር ዳር ከተማ የአባይ ወንዝ ላይ ተለዋጭ ድልድይ በአንድ ቢሊዮን 400 ሚሊዮን ብር በሆነ ወጪ ለመገንባት ዛሬ ተግባራዊ እንቅስቃሴው እንደሚጀመር ተገለጸ። ድልድዩ 380 ሜትር ርዝመት እንደሚኖረውና ወጪውም በመንግስት የሚሸፈን መሆኑን የኢትዮጰያ መንገዶች ባለስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ ለኢዜአ ተናግረዋል። ዳይሬክተሩ እንዳሉት የድልድዩ ግንባታ ሦስት ዓመታት ጊዜ እንደሚወስድና ስራውን የሚከናወነው በቻይናው ሲሲሲሲ የተባለው ተቋራጭ ድርጅት ነው። "የአባይ ወንዝ ተለዋጭ ድልድይ 43 ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን አማካሪ ድርጅቱም ተለይቷል "ብለዋል። አንድ ቢሊዮን 400 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚጠይቀው የድልድዩ ግንባታ ዛሬ ይጀመራል። በአሁኑ ወቅት ግንባታውን የማስጀመር ስነስርዓት እየተካሄደ መሆኑንና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ  ሪፖርተራችን ከስፍራው ዘግቧል። የባህር ዳር ጭስ አባይ የ22 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ ትናንት መጀመሩ በወቅቱ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም