በአዲስ አበባ በህገ-ወጥ መንገድ በ26 አይሱዙ ተሽከርካሪዎች ተጭኖ የነበረ የአትክልትና ኢንዱስትሪ ምርት ተያዘ - ኢዜአ አማርኛ
በአዲስ አበባ በህገ-ወጥ መንገድ በ26 አይሱዙ ተሽከርካሪዎች ተጭኖ የነበረ የአትክልትና ኢንዱስትሪ ምርት ተያዘ

መስከረም 7/2012 በአዲስ አበባ የአራዳ ክፍለ ከተማ ዛሬ ለሊት በተካሄደ የህገ-ወጥ ንግድ ድንገተኛ አሰሳ በ26 አይሱዙ ተሽከርካሪዎች ተጭኖ የነበረ የአትክልትና ኢንዱስትሪ ምርት መያዙን የክፍለ ከተማው አስተዳደር አስታወቀ። ግብረኃይል የተወሰደው የኦፕሬሽን ስራ ያለደረሰኝ ግብይት በሚፈፅሙ፣ያለንግድ ፍቃድ የሚነግዱ፣ ከአድራሻና መደብር ውጪ በሚነግዱ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሌላቸው የዋጋ ጭማሪባደረጉ ህገወጥ ነጋዴዎች ላይ የተወሰደ እርምጃ መሆኑም ተገልጿል። የአራዳ ክፍለ ከተማ ንግድ ፅህፈት ቤት ኃላፊአቶ ሃብታሙ ደሳለኝ እንዳሉት እርምጃው በጥናት ላይ ተመርኩዞ የተወሰደና በመደበኛ የንግድ እንቅስቃሴ ሳይሆን በጎዳናዎች ላይ ያለንግድፍቃድና ያለደረሰኝ ግብይት የሚፈፅሙ ነጋዴዎች ላይ ነው የተወሰደው። እርምጃው የተወሰደው ከደንብ፣ ንግድ፣ ገቢዎችእንዲሁም ከፖሊስ የተዋቀረ መሆኑንም ገልጸዋል። ነጋዴዎች ንግድ ፍቃድ እያለን ነው እቃዎቻችንየተወረሱት ብለው ያነሱት ጥያቄ ፍቃድ የሚሰጠው በተፈቀደላቸው መደብር እንዲሸጡ ቢሆንም የተገኙት ግን ከመደብር ውጪ ጎዳና ላይሲነግዱ መሆኑን አስረድተዋል። ለሊት ላይ በርካታ ነጋዴዎች ትክክለኛ መረጃናደረሰኝ ይዘው የተገኙት መኪናዎች ሳይሆን ደረሰኝ ሳይዙ ከመኪና መኪና ግብይት ሲፈፅሙ የነበሩ ናቸው ብለዋል። ምርቱ ከየት እንደመጣና በምን ያህል የተገዛእንደሆነ ሳይታወቅ ዋጋ ተተምኖ እየተሸጠ ነው ያሉት ኃላፊው ይህ ተግባር ህጋዊ ነጋዴውን ግብር ከፋዩን የሚጎዳ ፣ፀረውድድር፣ በህገወጥየተሰማሩት በአጭር ጊዜ እንዲበለፅጉ የሚያደርግ እንዲሁም ኀብረተሰቡ እየተደረገ ባለው የዋጋ ንረት ጫና ይደርስበታልና ይህን መሰረትተደርጎ በተዋቀረ ግብረ ኃይል የተወሰደ እርምጃ መሆኑንም ተናግረዋል። እርምጃው የተወሰደው በግብረኃይል መሆኑና በማንም ሰው ላይ የተወሰደ አላግባብ እርምጃ እንዳልነበርና ለተወረሰው ምርትም ህጋዊ ደረሰኝ የተሰጠና በመንግስት የአደራ አካውንት እየተቀመጡ መሆኑን ገልጸዋል። የተያዙት ምርቶች ሙዝ፣ ጤፍ፣በርበሬ፣ ዘይት፣አቮካዶ፣ድንችና ሰላጣን የመሳሰሉ የአትክልትና የኢንዱስትሪ ምርቶች መሆናቸውን አንስተዋል። ምርቶቹ ከተወረሱ በኃላ ለዩኒየኖች ተሰጥተው በሸማቾች ማህበር በኩል ለኀብረተሰቡ የሚቀርቡ መሆኑንም አንስተዋል። የፀረ ኮንትሮባንድና የህገወጥ ንግድ መከላከል የጋራ የግብረኃይል እቅድ ከሶስት ወር በፊት ታቅዶ ስራ የተጀመረ ሲሆን ላለፉት ሁለት ወራት በመደበኛ ሰዓት ሲሰራ መቆየቱንና በተደረገው ቁጥጥርም በርካታ ጥፋቶች ተገኝተው እርምጃ ሲሰወድ መቆየቱን አንስተዋል። የተወሰደው እርምጃም ያለ ደረሰኝ ግብይት፣ ከሚዛንጋር ተያይዞ የነበሩና ከዋጋ ጋር ተያይዞ የነበሩ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገሹና ገበያው እንዲረጋጋ ያስቻለ መሆኑን በመጠቆም። በቀጣይም ህገ-ወጦችን ቁጥጥሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ነጋዴውም ምርቶችን ሲገዛና ሲሸጥ በደረሰኝ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።