የክልሉን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ እየተሰራ ነው ---የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ - ኢዜአ አማርኛ
የክልሉን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ እየተሰራ ነው ---የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ
መስከረም 06/2012 የክልሉን ህዝብ ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝነት መጠበቅ የሚችል የፖሊስ ኃይል ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ ገለጸ። "አንድነታችንን በማጠናከር የክልላችንን ሰላምና ደህንነት እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ የፀጥታ አካላት ግምገማዊ ስልጠና ዛሬ በባህርዳር ከተማ ተጀምሯል። የቢሮው ኃላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገር ስልጠናው ሲጀመር እንዳሉት በተፈጠረው ጠንካራ የጸጥታ ኃይልም አጋጥሞ የነበረውን ችግር በማቃለል ክልሉን ማረጋጋት ተችሏል። የፀጥታ መዋቅሩ ክልላዊና ሀገራዊ ሁኔታውን ቀድሞ በመተንበይ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት መፈፀም እንዲችል የአቅም ግንባታ ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልፀዋል። አቶ አገኘሁ ሀገራዊ ለውጡ የሚመራበትን ሁኔታ በመገምገም ጠንካራ የሰላምና ደህንነት ስራ የሚቀጥልበት አቅጣጫ እንደሚቀመጥም ተናግረዋል። "አስተማማኝ ሰላም ደህንነት እንዲሰፍን መሰረቱ በየደረጃው ያለው የፖሊስ አካል ነው" ያሉት ደግሞ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ አበረ አዳሙ ናቸው።
ከሚሽነሩ እንዳሉት የክልሉ ፖሊስ በሳይንሳዊ መንገድ ታንጾና ዘመናዊ አሰራርን ተከትሎ እየተገነባ ነው። ህብረተሰቡ የሰላሙ ዋና ባለቤት ሆኖ እንዲያግዝም የፖሊስ ተግባር እንደሆነ ገልጸዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በበኩላቸው "ሰላም ሲታጣና ችግሮች በሚፈጠሩበት ወቅት ፈጥኖ ለህዝብ የሚደርሰው ፖሊስ ነው " ብለዋል። በክልሉ አጋጥሞ ከነበረው ቀውስ ፈጥኖ በመውጣት የተረጋጋ ሰላምና የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲያከናውን ምቹ ሁኔታ ተፈሯል። "ሰላማችንን ማረጋገጥና ማስጠበቅ ካልቻልን የተረጋጋ ክልል መፍጠር አንችልም "ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ የፖሊስ ኃይሉ ይህን በውል በመረዳትም ሰርቶ የማይደክመውን ታታሪ ህዝብ ሰላምና ደህንነቱ እንዲከበር በትጋት ማገልገል እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል። ፖሊስ የህግ አስከባሪ እንጂ የፖለቲካ መሳሪያ ሊሆን እንደማይገባ አመልክተው ያጋጠሙትን ውስብስብ ችግሮች ለመፍታት ተቋሙን በየደረጃው ሪፎርም የማድረግ ስራ እንደሚከናወን አስረድተዋል። ለስድስት ቀናት በሚቆየው ግምገማዊ ስልጠና በወቅታዊ አጀንዳዎች ዙሪያ እንደሚያተኮር ተገልጿል።