ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አውሮፕላን አብራሪዎች ማኅበር ከተመሰረተ ረጅም እድሜ ቢያስቆጥርም ጉልህ ተግባር አላከናወነም

መስከረም 6/2012  የኢትዮጵያ አውሮፕላን አብራሪዎች ማኅበር ከተመሰረተ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ቢያስቆጥርም የተቋቋመበትን ዓላማ ለማስፈጸም ግን ጠንካራ ስራዎቸን አለማከናወኑን አስታውቋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን እንደ ማኅበር የሚጠበቅበትን ተግባር ለመፈጸም እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውቋል። የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ካፒቴን የሺዋስ ፈንታሁን ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ማኅበሩ በ1953 ዓ.ም ሲቋቋም በሙያዊ ጉዳዮች ለመወያያት አባላቱን በሙያው ለማሳደግና የጋራ ጥቅም ለማስከበር በማለም ነው። አሁን ላይ ከ750 በላይ አባላት ያሉት ማኅበሩ ከተመሰረተ ግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ እድሜ ቢሆነውም ቅሉ፤ የሚጠበቅበትንና የተቋቋመበትን ዓላማ ከማሳካት አንጻር ግን የሰራው ስራ አለመኖሩን ተናግረዋል። ከቅረብ ጊዜ ወዲህ ግን አባላቱን የማነቃቃት፣ ለሙያው ክብር እንዲሰጡና በሙያው ራሳቸውን እንዲያጎለብቱ የሚያስችል ስራዎች መጀመሩን አስታውቀዋል። በቀጣይም ደግሞ በማኅበራዊ መስኮች ማኅበረሰቡን ማገልገል በሚቻልባቸው ተግባራት ላይ ለመሳተፍ እንቅስቃሴ መጀመሩንም ተናግረዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም