ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ለኢትዮጵያ አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ መስከረም 1/2012 አዲሱ ዘመን ሰላም ፍቅር እና አንድነትን ለሁላችንም እንዲያመጣል እመኛለሁ ሲሉ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር አልስቴር ማክፔል ገለጹ። አምባሳደሩ የ2012 ዓ.ም የዘመን መለዋጫን አስመልክቶ በአማርኛ ቋንቋ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። አምባሳደር አልስቴር ማክፔል ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለአዲሱ ዓመት እንኳን በሰላምና በጤና አደረሳችሁ ብለዋል። "አዲሱ ዘመን ሰላምን ፍቅርና አንድነትን እንዲያመጣ እመኛለሁ" ያሉት አምባሳደሩ እንኳን ለ2012 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል አደረሳችሁ በማለት የመልካም ምኞት መግለጫቸውን አስተላልፈዋል። ለኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ማለታቸውን ከኢምባሲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ኢዜአ ያነጋገራቸው አምባሳደሮች አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት የሰላም፣ የደስታ፣ የስኬትና ብልዕግና እንዲሁም የአገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት የሚጠናከርበት ይሆን ዘንድ ምኞታቸውን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ታን ጂያን፣ የህንድ አምባሳደር አኑራግ ስሪቫስታቫ፣ የቱርክ አምባሳደር ሚስ ያፕታክ አልፕ፣የሜክሲኮ አምባሳደር ቪክቶር ማኑኤል ትሬቪኖና የሰርቢያ አምባሳደር አሌክሳንደር ሪስቲች የአዲስ ዓመት የመልካም ምኞች መልክት አስተላልፈዋል። በተጨማሪም በኢትዮጵያ የአርጀንቲና ፣ ሩዋንዳ ፣ ደቡብ ኮሪያ ፣ ፓኪስታን ፣ አዘርባጃንና አየርላንድ አምባሳደሮች የአዲስ ዓመት የመልካም ምኞት መግለጫቸውን ያስተላለፉ ሲሆን አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የስኬትና የብልጽግና እንዲሆን ተመኝተዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም