ህዝቡ በአዲሱ ዓመት አንድነቱን አጠናክሮ ለክልሉ ልማት እንዲረባረብ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ጥሪ አቀረቡ

96
ጷጉሜ 6/2011 ህዝቡ በአዲሱ ዓመት አንድነቱን አጠናክሮ ሰላሙን በመጠበቅ ለክልሉ ልማት መፋጠን በጋራ እንዲረባረብ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መሰተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ጥሪ አቀረቡ:: ርዕሰ መስተዳድሩ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለኢዜአ እንደገለጹት የክልሉ መንግስት በአዲሱ ዓመት የህዝቡን የልማት ፍላጎቶች ለማሟላት የሚያግዙ በርካታ እቅዶችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ለእቅዶቹ ስኬታማነት ሁሉም ህብረተሰብ ከመንግስት ጎን በመሰለፍ በየተሰማራበት የሙያ ዘርፍ የድርሻ መወጣት እንዳለበት አመልክተዋል። በአዲሱ ዓመት በተለይም እንደ ሀገር የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ በማስቀጠል ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ሁሉም ዜጋ ጠንክሮ እንዲሰራም አውስተዋል። ህዝብ  አንድነቱን አጠናክሮ ሰላሙን በመጠበቅ ለክልሉ ልማትና እድገት መፋጠን በጋራ ርብርብ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል። አዲሱ ዓመት ለመላው የክልሉና የኢትዮጵያ ህዝብ የሰላም፣ የጤናና  የብልጽግና ዘመን እንዲሆን ርዕሰ መስተዳደሩ መልካም ምኞታቸውንም ገልጸዋል።                
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም