ቀጥታ፡

የአገር መከላከያ ሰራዊት የምስራቅ ዕዝ የዘመን መለዋጫ በዓልን እያከበረ ነው

ጳግሜ 4/2011የአገር መከላከያ ሰራዊት የምስራቅ ዕዝ የዘመን መለዋጫ በዓልን በሐረር ከተማ እያከበረ ነው። በዓሉ እየተከበረ የሚገኘው "ለሕገ መንግስቱ ፍጹም ታማኝ በመሆን በአዲሱ ዓመትም ግዴታችንን በላቀ ውጤት ለመፈጸም ዝግጁ ነን" በሚል መሪ ሃሳብ ነው። የክልሎች ፕሬዚዳንቶች እና የአገር መከላከያ ሰራዊት የቀድሞ አዛዦች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በበዓሉ ላይ ለመታደም ሐረር ከተማ ገብተዋል። በበዓሉ ላይ ከፍተኛ የአገር መከላከያ ሰራዊት አዛዞችን ጨምሮ የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። የሰራዊቱ የተለያዩ እዞች የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት (የዘመን መለዋጫ) በዓል በየዓመቱ ከህዝቡ ጋር እንደሚያከብሩ ይታወቃል። የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ ለ2012 አዲስ ዓመት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል። በመልእክታቸውም "ኢትዮጵያ የሁላችንም ብቸኛ ቤት፤ የሁላችንም መኩሪያና መድመቂያ በመሆኗ መላው ህዝባችንና የመከላከያ ሰራዊታችን በዚህ መርህ ዕጅ ለዕጅ ተያይዘን እንዝለቅ" በማለት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም