ብሄራዊ የኩራት ቀን በታላቅ ስነ-ስነሰርዓት እየተከበረ ነው 

ጷጉሜ 3/2011 ብሄራዊ የኩራት ቀን በታላቅ ስነ-ስነሰርዓት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተለያዩ ትእይንቶች እየተከበረ ነው።

በትርኢቱ ላይ ከ250 ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የታደሙ ሲሆን የከተማው ነዋሪዎችም የተለያዩ የአገር ታሪክንና ባህልን የሚያንፀባርቁ ትርኢቶችን በሰልፍ አሳይተዋል።

የመከላከያና የፖሊስ ሰራዊት አባላትም ወታደራዊ ሰልፍ አቅርበዋል።

የከተማው ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ለብዙ ዓመታት ያቆያት የህዝቦች አንድነት መሆኑን ጠቅሰው "የአገሪቱ ብሄራዊ ኩራትም የህዝቦቿ በአንድነት ነው" ብለዋል።

በርካታ ተማሪዎች፣ ወጣቶች፣ አባት አርበኞች፣ አንጋፋ አትሌቶችና ሌሎችም የታደሙበትን የዘንድሮ ኩራት ቀን ከተለያዩ አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነው።

ከጳጉሜ 1 ቀን 2011 ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት በኢትዮጵያ ሰላም፣ ብሄራዊ አንድነት፣ ብልፅግና፣ ሀገራዊ ኩራት፣ ዴሞክራሲንና ፍትህን በመላው ዜጎች በማስረፅ ተጠቃሚ መሆን የሚቻልበትን ሁኔታ ለማጠናከር የሚያግዙ ኩነቶች በመካሄድ ላይ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም