የሐብሊ ሊቀመንበር የመልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውን ድርጅታቸው አስታወቀ

ሀረር  ሰኔ 7/10/2010 የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ/ሐብሊ/  ሊቀመንበር የመልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውን ድርጅታቸው አስታወቀ፡፡ ሐብሊ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ   የድርጅቱ ሊቀመንበር ያቀረቡትን  የመልቀቂያ ጥያቄ በመርህ ደረጃ ችግር እንደሌለበት ነው ያመለከተው፡፡ የመልቀቂያውን ጉዳይ በመገምገም ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ሁኔታዎችን  በማመቻቸት በሂደት ተግባራዊ እንዲሆን አቅጣጫ መቀመጡን አስታውቋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የሐብሊ ማዕከላዊ ኮሚቴ  ሰኔ 2/ 2010ዓ.ም. በሐረር ከተማ  ነውጠኞች ቡድኖች ባላቸው በተፈጸመ   ጥቃት በሰው ላይ በደረሰው የአካል መቁሰልና የንብረት  ጉዳት በጽኑ አውግዟል፡፡ ድርጊቱ ሐብሊን እና ኦህዴድን የማይወከል የጸረ ሰላም ኃይሎች እንቅስቃሴ መሆኑን  ጠቅሶ  አጥፊዎችን በህግ መጠየቅ እንዳለባቸው ማዕከላዊ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡ ሁከትን  እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ጥቂት ግለሰቦች ፍላጎታቸውን ለማራመድ ከጀመሩት ህገ ወጥ እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡም አሳስቧል
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም