ቀጥታ፡

ወጣቱ የዲጂታል ዓለም ቴክኖሎጂን ለአዎንታዊ ተግባር እንዲያውለው በትኩረት መስራት ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ  ነሀሴ 29/2011 ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች የዲጂታል ዓለም ቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን ለአዎንታዊ ዓላማ ብቻ እንዲጠቀሙበት ለማድረግ የሚያስችል ግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራትን ማካሄድ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አሳሰበች። በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ‘የአፍሪካ የወጣቶችን ዲጂታል ቴክኖሎጂ ፈጠራና ሁለንተናዊ ዕድገት ማበረታቻ' ጉባኤ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ተጀምሯል። ለመጪዎቹ 4 ቀናትየሚካሄደውጉባኤየሮማውካቶሊካዊትቤተ-ክርስቲያንርዕሰ-ሊቃነጳጳሳትአባፍራንሲስ፤አፍሪካውያንወጣቶችየማህበራዊ ሚዲያን ጨምሮ ሌሎች ዲጂታልዓለምቴክኖሎጂዎችን ለመልካምተግባርያውሉትዘንድለማሳሰብየጀመሩትአህጉራዊጉብኝትአካልነው። አባ ፍራሲስ ይህንኑ መልዕክታቸውን ለማስተላለፍ ያለመውን ጉብኝታቸውን በአሁኑ ወቅት በሞሪሸስ፣ማዳጋስካርናሞዛምቢክበማድረግላይመሆናቸውምታውቋል። ተግባቦትየሰው’ነትመገለጫናየዕምነቱቀኖናመሆኑንያነሱትየኢትዮጵያካቶሊካዊትቤተ-ክርስቲያንካርዲናልሊቀ-ጳጳስብፁዕአቡነ ብርሃነ እየሱስ በጉባኤው ላይ ባስተላለፉት መልዕክትየዲጂታልቴክኖሎጂአጠቃቀምንበተመለከተብዥታአለ። ድረ-ገጾችንና ማህበራዊ ሚዲያን ጨምሮ አያሌ ትሩፋቶች ካሉት የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በወጣቱ ዘንድ ያለውን ይህንን ብዥታ በመለወጥ ዘርፉን ለፈጠራና ሌሎች አዎንታዊ አገልግሎቶች መጠቀም ይቻል ዘንድ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮች መተግበር አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል። በዚህ ረገድ ጉባኤው በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በተለይ ለወጣቶች መዘጋጀቱ ወቅታዊና ጠቃሚ መሆኑንም ጠቁመዋል። ወጣቱ ተገቢውን ቴክኖሎጂ ለተገቢው አገልግሎት እንዲያውል ለማሳሰብ ጉባኤው የበኩሉን ሚና ይጫወታልም ብለዋል። የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተ-ክርስያን ወጣቶች አስተባባሪ ሲስተር ሰላም ብርሃኑ፤ ቴክኖሎጂውን በተለይም ማህበራዊ ሚዲያውን ከመጠቀም ጋር በተያያዘ በአሁኑ ወቅት የሚስተዋለው ችግር ምንጩ የግንዛቤ እጥረት ነው ሲሉ ለኢዜአ ገልፀዋል። ወጣቱ በማህበራዊሚዲያ የሚሰራጭ መረጃን እንደወረደ ከመቀበል ይልቅ የመረጃውን ትክክለኛነት የማመሳከርና የማስተንተን ልምድን እንዲሁም ምክንያታዊአስተሳሰብን እንዲያዳብር መደረግ አለበትም ብለዋል። ኢትዮጵያን ጨምሮ አፍሪካዊያን ወጣቶች የዲጂታል ዓለሙን ቴክኖሎጂ ትሩፋቶች አዎንታዊ ለሆኑ ዓላማዎች ብቻ መጠቀም የሚችሉበትን ሁኔታ የማመቻቸት ዓላማን ባነገበው ጉባኤው ላይ ከመላውአህጉሪቱየተውጣቱከመቶበላይየቤተ-ክርስቲያኗተወካዮችተገኝተዋል። ከጉባኤው ጎን ለጎንም ታዳሚዎቹ በአዲስ አበባ ብሔራዊ ሙዝየምን ጨምሮ የተለያዩ ታሪካዊ ቦታዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም