የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ላይ ውሳኔ ተሰጠ

55
ነሐሴ 29 / 2011 የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት ላይ ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት ውሳኔ አሳለፈ። ሚኒስቴሩ በፈተናው እስካሁን ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ባደረገው ጥናት ማረጋገጡንም አስታውቋል። ሚኒስቴሩ፣ የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲና የክልል ትምህርት ቢሮዎች በጋራ በሰጡት መግለጫ በፈተናው ያጋጠመውን ችግር ኮሚቴ ተቋቁሞ ሲመረምር መቆየቱን ገልጸዋል። በዚሁ መሰረት በተፈጥሮና በማህበራዊም ሆነ በሳይንስ መስኮች ሰኔ 6 እና 7 ቀን 2011 ዓ.ም ፈተናቸው የተሰጡ የትምህርት አይነቶች ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ታሳቢ የተደረጉ ሲሆን ሰኔ 10 እና 11 ቀን የተሰጡ ፈተናዎች  ውጤቶች  ግን ተሰርዘዋል። ሰኔ 6 እና 7 የተሰጡ የትምህርት አይነቶች ለዩኒቨርስቲ መግቢያ እንዲያገለግሉ የተወሰነው ሂሳብ፣ እንግሊዝኛ፣ ፊዚክስ፣ አፕቲትዩድ እና ጂኦግራፊ ናቸው። ሰኔ 10 እና 11 ቀን 2011 ዓ.ም የተሰጡ ፈተናዎች ከግምት ውስጥ ያልገቡት እጅግ የጋሸበ ውጤት የተመዘገበባቸው በመሆኑ እንደሆነ ተገልጿል።          
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም