የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ 31ኛ ዓመት በዓለ ሲመት እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ 31ኛ ዓመት በዓለ ሲመት እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ ኢዜአ ነሃሴ 29/2011 አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ 31ኛ ዓመት በዓለ ሲመት በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ነው። በበዓለ ሲመቱ ላይ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘ አክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሐይማኖትን ጨምሮ የየአገረ ስብከቱ ሊቀጳጳሳትና የየአጥቢያው አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች ተገኝተዋል። በዓለ ሲመቱ እየተከበረ ያለው በመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ነው። አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ላለፉት 20 ዓመታት አሜሪካን አገር የሚገኘውን 'ስደተኛ ሲኖዶስ' እየተባለ የሚጠራውን መንበር ሲመሩ እንደነበርና በቅርቡም በተፈጠረው እርቀ ሰላም ወደ አገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።