ቀጥታ፡

እስካሁን በአግባቡ መልማት ያልቻለውን የቱሪዝም ዘርፍ ለመለወጥ መንግስት ከምን ጊዜውም በላይ በትኩረት እየሰራ ነው

ነሀሴ 28/2011 እስካሁን በአግባቡ እንዲለማ ተደርጎ ጥቅም ላይ ያልዋለውን የቱሪዝም ዘርፍ ለመለወጥ መንግስት ከምን ጊዜውም በላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ። የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የሆቴልና ቱሪዝም ኮንፈረንስ "ቱሪዝም ብሩህ ተስፋ ለኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ይገኛል። በጉባኤው ላይ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛል። በጉባኤው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እንደገለጹት፤ መንግስት ለቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል። እስካሁንም በአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ውስጥ ቱሪዝም አንዱ እንዲሆን ተወስኖ በከፍተኛ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። የዘርፉን ችግሮች ለመፍታትም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውንም ገልጸዋል። በጉባኤው ላይ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ያተኮሩ ውይይቶች እንደሚደረጉ ይጠበቃል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም