ባህማስ ዶርያን በተሰኘው አውሎ ንፋስ ተመታች

106
ኢዜአ ነሃሴ 27/2011 ሃይለኛ የተባለው አውሎ ንፋስ ከካሬቢያን ደሴቶች አንዷ የሆነችውን ባህማስ በመምታት የቤቶች ጣርያ አፈራርሷል ሃይለኛ ጎርፍም አስከትሏል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው ዝግ ብሎ የሚንቀሳቀሰውና አምስተኛው አይነት የዶርያን አውሎ ንፋስ በአትላንቲክ ላይ በሪከርድ በሁለተኝነት መመዝገቡንና በሰአት 250 ኪሎ ሜትር እየነፈሰ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ለህይወት አስጊ እንደሆነ የተገለፀው አውሎ ንፋስ ሰባት ሜትር ወደ ፊት የሚወነጨፍ መሆኑም ነው የተነገረው፡፡ ዝግ እያለ ወደ ፊት እየገፋ ያለው አውሎ ንፋስ ወደ ምስራቃዊ የአሜሪካን የባህር ዳርቻዎችን ሊመታ ይችላል የሚል ስጋት ቀስቅሷል፡፡ በዚሁ ምክንያት ፍሎሪዳ፣ጆርጅያ ሰሜንና ደቡብ ካሊፎርንያ የአሜሪካ ግዛቶች የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አውጀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም