የሳዑዲ ልዑል መሃመድ ቢን ሰልማን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር በስልክ ተነጋገሩ

104
ነሀሴ 13/2011 የሳዑዲ አረቢያ ልዑል መሃመድ ቢን ሰልማን ቢን አብዱላዚዝ ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በስልክ ተነጋግረዋል፡፡ ልዑሉ በተለይ የሱዳን ተቀናቃኝ ሀይሎች ወደ አንድ እንዲመጡ ኢትዮጵያ እየተጫወተች ያለውን ሚና አድንቀዋል፡፡ ለዚህም የሳዑዲ መንግሥት በአካባቢው ለሚደረገው ማንኛውንም የማረጋጋትና ሰላም የማስፈን ተግባር ድጋፍ እንደሚያደርግ መናገራቸውን  የሳዑዲው ፕሬስ ኤጀንሲ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም