ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ 105 እስረኞችን ከሱዳን ይዘው ተመለሱ

አዲስ አበባ ነሃሴ 12/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በስደት ወደ ተለያዩ አገራት ለመውጣት ሞክረው በሱዳን አገር እስር ላይ የነበሩ 105 እስረኞችን ይዘው ተመለሱ። የተቀናቃኝና ወታደራዊ ኃይላት ለሚመሰርቱት የሽግግር መንግስት የፊርማ ስነ-ስርዓት ለመታደም ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት ማምሻውን ተመልሰዋል። ወደ ካርቱም ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከተልዕኳቸው በተጓዳኝ በአገሪቷ በተለያዩ እስር ቤቶች ቆይተው በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተጠለሉ 105 ስደተኛ እስረኞችን ነው ይዘው የተመለሱት። ስደተኞቹ ሱዳንና ሊቢያን በመተላለፍ ወደ ተለያዩ የአውሮፓና አረብ አገራት ለመሻገር በደላላ ተታለው ከአገር የወጡና አስከፊ የስደት ቆይታ የነበራቸው ናቸው። ከጥቂት ወንድ እስረኞች በስተቀር ስደተኞቹ አብዛኞቹ ሴቶች ናቸው። ስደተኞቹ ወደ ትውልድ አገራቸው በመመለሳቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና አቅርበዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም