የሲዳማ ብሔር ቋንቋና ባህል ሲምፖዚየም በሃዋሳ ከተማ ተከፈተ

82
ነሐሴ 10/2011  25ኛው የሲዳማ ብሔር ቋንቋና ባህል ሲምፖዚየም ዛሬ በሃዋሳ ከተማ ተከፈተ ። በሲምፖዚየሙ ላይ ከሲዳማ ዞን ወረዳዎች የተወጣጡ የባህል አባቶች፣ የክልልና ፌደራል ባለስልጣናትና የሚመለከታቸው አካላት እየተሳተፉ ነው። በሲምፖዚየሙ የብሔረሰቡን ባህላዊ መስተጋብሮች የሚገልጹ ቁሳቁስ፣ አልባሳትና ምግቦች ለእይታ ቀርበዋል ። በብሔረሰቡ ቋንቋና ባህል ላይ የተሰሩ ጥናታዊ ፅሁፎችም ቀርበው ውይይት እየተካሄደባቸው ነው። የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ሌዳሞ በወቅቱ እንደገለፁት ሲምፖዚየሙ  የብሔረሰቡን ቋንቋና ባህል ለማስተዋወቅና ለማሳደግ እየተከናወኑ ካሉ ተግባራት አንዱ ነው ። ላለፉት 25 ዓመታት የብሔሩን ቋንቋና ባህል ለማስተዋወቅና ለማሳደግ በተሰሩ ሥራዎች አበረታች ወጤቶች ተመዝገበዋል” ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፣  የብሔሩን የዘመን መለወጫ ፍቼ ጨንበላላ በዓልን ከሁለት ዓመት በፊት በዓለም ቅርስነት ማስመዝገብ መቻሉን ለአብነት ጠቅሰዋል ።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም