የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኡጋንዳ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላትን አወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኡጋንዳ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላትን አወያዩ
አዲስ አበባ ኢዜአ ነሀሴ 10/2011 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በኡጋንዳ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላትን አወያዩ። በውይይቱ የማህበረሰቡ አባላትና በአገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ተገኝተዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው፣ የመከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሣ ፣ በኡጋንዳ የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዓለምፀሐይ መሠረት በካምፓላ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላትን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ አወያይተዋል። ከኢትዮጵያዊያኑ ጋር ያደረጉት ውይይት በአገሪቱ እየተካሄደ ባለው ለውጥ ዙሪያ እንዲሁም በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ በውይይቱ የማህበረሰቡ አባላት ባነሷቸው ሃሳቦቸ ዙሪያ ምላሽ ተሠጥቷል።
ኢትዮጵያዊን በጋራ ሆነው ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በጋራ እየተወጡ በአገሪቱ የተጀመረውን ለውጥ ዳር ለማድረስ መረባረብ እንደሚያስፈልግም ትኩረት ተሰጥቶበታል። በኡጋንዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን አገራዊ ለውጡን ለመደገፍም ቃል ገብተዋል፡፡ ውይይቱ ከሶስተኛው የኢትዮ-ኡጋንዳ የሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን የተካሄደ ነው።
ኢትዮጵያዊን በጋራ ሆነው ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በጋራ እየተወጡ በአገሪቱ የተጀመረውን ለውጥ ዳር ለማድረስ መረባረብ እንደሚያስፈልግም ትኩረት ተሰጥቶበታል። በኡጋንዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን አገራዊ ለውጡን ለመደገፍም ቃል ገብተዋል፡፡ ውይይቱ ከሶስተኛው የኢትዮ-ኡጋንዳ የሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን የተካሄደ ነው።