የኤሌክትሪክ ሰራተኛው በተሳሳተ መረጃ ከመገደል ለጥቂት ተረፈ - ኢዜአ አማርኛ
የኤሌክትሪክ ሰራተኛው በተሳሳተ መረጃ ከመገደል ለጥቂት ተረፈ
ነሀሴ 7 /2011 በደቡበ ወሎ ዞን ጃማ ወረዳ በተሳሳተ መረጃ በመንጋ ውሳኔ ሊገደል የነበረው የመብራት ሃይል ሰራተኛ በፖሊስ ድጋፍ ህይወቱን ማትረፍ ተችሏል ። በዞኑ የጃማ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ኢንስፔክተር ተሾመ ለገሰ ለኢዜአ እንደገለፁት ትናንት ከሰዓት በኋላ አንድ የፌዴራል ኤሌክትሪክ ሃይል ሰራተኛ ከዓለም ከተማ ወደ ቃስታ የተዘረጋውን መስመር በማስተካከል ስራ ላይ ተሰማርቶ ነበር ። ሰራተኛው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ መረጃ ለመሰብሰብና የተበላሹ መስመሮቹን ለማስተካከል የተሰማራ ቢሆንም የህፃናት ኩላሊት ለመስረቅ የመጣ ነው የሚል የተሳሳተ መረጃ በመናፈሱ ምክንያት የአካባቢውን ህዝብ ለደቦ ውሳኔ እንዲነሳሳ አድርጎታል ። በወረዳው የ017 ቀበሌ ህዝብ ተሰባስቦ ወንጀል ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ የአካባቢው ፖሊስ በፍጥነት ደርሶ ህይወቱን እንዳተረፈው ኢንስፔክተሩ ገልፀዋል ። ሰራተኛውበህይወትተርፎበፖሊስከለላስርከዋላበኋላምበጉልበትነጥቀውለመግደልየሞከሩአምስትሰዎችበቁጥጥርስርእንዲውሉተደርጓል። ጥቂት ግለሰቦች በነዙት አሉባልታ ተነሳስቶ የሰው ህይወት ለመቅጠፍ መንቀሳቀስ ተገቢነት እንደሌለው የገለፁት ሃላፊው ሰራተኛው በማያውቀው ምክንያት ከመገደል የተረፈው ለጥቂት ነው ተብሏል ። ህብረተሰቡ ለወደፊቱም ቢሆን በተሳሳተመረጃ ወደ ጥፋት በመግባት የህግጥሰትእንዳይፈጸምዛሬበደጎሎከተማ የምክክር መድረክ ተካሔዷል ። በመድረኩ ላይ ህብረተሰቡበተሳሳተመረጃ ተነሳስቶ ወደ ደቦፍርድ ከመግባት እንዲቆጠብ ትምህርት ተሰጥቷል ። አጠራጣሪ ጉዳይ ቢያጋጥም እንኳን ለፀጥታ ሃይሎች መጠቆም እንጂ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ወንጀል መፈፀም ከተጠያቂነት እንደማያድን በአፅንኦት ተነግሯል ። ሀብረተሰቡ ከውይይቱ በኋላ ሰራተኛውን በይፋ ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን ለወደፊቱም ከአሁኑ ስህተት በመማር በስሜት ወደ ወንጀል ከመነዳት እንደሚጠነቀቅ ቃል ገብቷል ። በአካባቢው ፖሊስ ድጋፍ ህይወቱን የተረፈው ማቱሳላ መንግስቱ የተባለው ሰራተኛ የህብረተሰቡን ይቅርታ ተቀብሎ ፖሊስ ህይወቱን ስላተረፈለት ምስጋናውን አቅርቧል ። መጠነኛ ድብደባ ከማጋጠሙ በስተቀር የከፋ ጉዳት ስላልደረሰበት በነገው እለት ወደ መደበኛ ስራው እንደሚመለስም አስረድቷል ። ባላሰበበት መንገድ ከሞት አፋፍ መትረፉን አስመልክቶ እለቱን ዳግም የተወለደበት ቀን አድርጎ እንደሚመለከተው በመግለፅ ከዚህ ከተረፍኩኝ ረጅም ዕድሜ ይኖረኛል የሚል ተስፋ እንድሰንቅ አድርጎኛል ብሏል ። በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቡ ወረዳ በቅርቡ ህጻን ሊሰርቁ የመጡ ናቸው በሚል የተሳሳተ መረጃ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ኢዜአ መዘገቡ ይታወሳል፡፡