የመንግስት የፋይናንስ ሪፎርም በትናንሽ ቢዝነሶች ለሚፈጠሩ የስራ እድሎች ይበልጥ ተደራሽ መሆን አለበት - ኢዜአ አማርኛ
የመንግስት የፋይናንስ ሪፎርም በትናንሽ ቢዝነሶች ለሚፈጠሩ የስራ እድሎች ይበልጥ ተደራሽ መሆን አለበት
አዲስ አበባ ኢዜአ ነሃሴ 6/2011 የመንግስት የፋይናንስ ሪፎርም በትናንሽ ቢዝነሶች ለሚፈጠሩ የስራ እድሎች ይበልጥ ተደራሽ መሆን እንዳለበት ተጠቆመ። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት 'አዲስ ወግ' በሚል ርእስ በየወሩ የሚያዘጋጀው የውይይት መድረክ ዛሬ ትኩረቱን የስራ አድል ፈጠራ ላይ አድርጎ ተካሄዷል። በመድረኩ የግልና የመንግስት ሴክተርን የወከሉ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ለውይይቱ የመነሻ ሃሳብ አቅርበዋል። የውይይቱ ዋነኛ ዓላማም ለመንግስት ፖሊሲ አፈጻጸም ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦችን መጠቆም ሲሆን፤ የተለያዩ የፋይናንስ ተቋማትን የወከሉ ግለሰቦች በመድረኩ ተሳትፈዋል። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ መሳይ ታደሰ በዚህን ወቅት እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ ብቻ በዓመት 500 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል። በተጨማሪም በኢትዮጵያ 55 ሺህ የሚሆኑ ማህበራዊ ኢንተርፕራይዞች እንዳሉ ጠቁመው፤ እያንዳንዱ ኢንተርፕራይዝ በአማካኝ ለሃያ አንድ ሰው የስራ እድል ይፈጥራል ብለዋል። ከተጠቀሱት ኢንተርፕራይዞች መካካል 60 በመቶ የሚሆኑት የፋይናንስ አቅርቦት ችግር እንዳለባቸውም ግን አልሸሸጉም። በኢትዮጵያ በተናጥል ማህበራዊ ኢንተርፕራይዞችን ብቻ የሚመለከት የህግ ማእቀፍ አለመኖሩ ደግሞ ሌላኛው ማነቆ መሆኑን በመጠቆም። በመሆኑም የፋይናንስ ተደራሽነቱ እስከ ዝቅተኛው የቢዝነስ መዋቅር ሊሰፋ ይገባል መልዕክታቸው ነው። አቶ ብሩክ ፍቅሩ በበኩላቸው የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ስፋትና ውጤታማነት በእያንዳንዱ ዜጋ የኑሮ መሻሻል ሊመዘን እንደሚገባ ይናገራሉ።
የአገሪቷ የፋይናንስ ስርዓት ዜጎች ሰርተው የሚቆጥቡት ገንዘብ ዋጋውን ጠብቆ እንዲቆይ የማድረግ አቅም ሊኖረው እንደሚገባም አውስተዋል። ይህም ባንክን ጨምሮ በፋይናንስ ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን በመፍታት ረገድ ሚናው የጎላ መሆኑን በመጠቆም። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ አማካሪ አቶ ማሞ ምህረቱ መንግስት የዜጎችን ሁለገብ የኑሮ ማሻሻልን ያለመ የኢኮኖሚ ፕሮግራም ሰነድ ማዘጋጀቱን ተናግረዋል። የሚንስትሮች ምክር ቤት ጉዳዩን በሚመለከት ያስቀመጠው አቅጣጫና ሌሎች ዝርዝር የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በሰነዱ መካተታቸውንም ጠቁመዋል። ሰነዱን የሚመለከት የባለድርሻ አካላት ውይይት በቅርቡ እንደሚጀመርም ገልጸዋል። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የተጋረጡ ችግሮችን ለመፍታት መንግስት "ማክሮ፡ መዋቅራዊና ሴክተራል" የሚሉ ሪፎርሞችን እያከናወነ መሆኑንም አቶ ማሞ አብራርተዋል። ሪፎርሙ በተለይ ዝቅተኛውን የህብረተሰብ ክፍል የብድር ተጠቃሚ እንደሚያደርግም አክለዋል። በዜጎች የስራ እድል ፈጠራ ላይ ዋነኛ ተዋናይ ለሆነው የግሉ ዘርፍ የሚደረገው የብድር አቅርቦት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተናገሩት ደግሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ባጫ ጊና ናቸው። ባንኩ ባለፈው በጀት ዓመት 22 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ብድር ለግሉ ዘርፍ መስጠቱንም ለአብነት አንስተዋል። መንግስት በ2012 በጀት ዓመት ለ3 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ማቀዱን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።