የአክሱም ከተማ ሙሰሊም ማህበረሰብ ሰላሟ የተጠበቀና የተረጋጋች አገር ለመፍጠር በሚደረገው እንቅስቃሴ ድርሻውን እንዲወጣ ተጠየቀ

93
አክሱም ነሐሴ 05/ 2011 ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሰላሟ የተጠበቀና የተረጋጋች አገር ለመፍጠር በሚደረገው እንቅስቃሴ ድርሻውን እንዲወጣ የአክሱም ከተማ እስልምና ጉዳዮች ሊቀመንበር አሳሰቡ። የኢድ አልአድሃ አረፋ 1440ኛው በዓል በአክሱም ከተማ ዛሬ ተከብሯል። ሊቀመንበሩ አቶ አብደላ ሐጂ ሙስጠፋ በበዓሉ ላይ እንዳስገነዘቡት ሕዝበ ሙስሊሙ መንግሥት ለሚያደርገው የሰላምና የልማት እንቅስቃሴ ከጎኑ መቆም ይገባዋል። የኢድ አልሃ አድሃ ጨምሮ የተለያዩ በዓላትን ያከበርነው ሰላምና መረጋጋት በመኖሩ ነው ያሉት ሊቀ መንበሩ፣ አሁንም ከመንግሥት ጎን በመቆም ለሰላማችንና ለአገራችን እድገት እንሰራለን ብለዋል። ሙስሊሙ ማህበረሰቡ በዓሉን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳትና በአንድነት የመኖር ባህሉን ማጠናከር እንደሚገባውም አሳስበዋል። የበዓሉ ተሳታፊ የሆኑት አቶ በሽር ጥዑም በዓሉን በደስታ እያከበሩት መሆኑን ገልጸው፣የአገርን ሰላምና ደህንነትን ለማስቀጠል እንደሚሰሩ ገልጸዋል። በአገሪቱ ሰላም ባይኖር ኖሮ፤በዓሉን ማክበር አንችልም ነበር፣ኅብረተሰቡ ለራሱ ሲል ሰላሙን ማስጠበቅ አለበት ብለዋል ። በከተማው የሓየሎም ቀበሌ ነዋሪ አቶ መሐመድ በሽር በበኩላቸው በዓሉ በመከባበርና በአንድነት እንዲሁም የተቸገሩ ወገኖች በመርዳት እያከበሩት መሆናቸውን ተናግረዋል።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም