ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሜቴ ጠቅላላ ጉባኤውን በደብረ ብረሀን ከተማ ጀመረ

ደብረ ብርሀን (ኢዜአ) ነሃሴ 4 ቀን 20011- የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሜቴ 44ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ዛሬ በደብረ ብርሀን ከተማ ማካሄድ ጀመረ። ጉባኤው በጧቱ ውሎ የ2011 በጀት ዓመት የፅራ አፈጻጸም በመገምገም በአንድ ድምጽ ታቅቦ አፅድቋል ። ከቀትር በኋላ በሚኖረው ውሎም በ2012 ዓ.ም እቅድ አቅጣጫ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ ኦሎፒክ ኮሜቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ “ጉባኤው የኢትዮጵያ ህዝብን የስፖርት ባለቤትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቃል የምንገባበት ነው” ብለዋል። በተያዘው በጀት ዓመት 3 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኦሎፒክ ደጋፊዎችን ለመመዝገብ ከክልልና ከከተማ አሰተዳደሮች ጋር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሒሩት ካሳው ስፖርት አርትም ሳይንስም በመሆኑ እያደረገ መምጣቱን ተናግረዋል ። “ዘርፉ ህዝባዊ መሰረት እንዲይዝ ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል “ ያሉት ሚኒስትሯ፣ በበጀት ዓመቱ ዘርፉን ለማሳደግ በመንግስት ልዩ ትኩረት መሰጠቱን ጠቁመዋል ። የኢትዮጵያ ኦሎፒክ ኮሜቴም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል ። የደብረ ብርሃን ከተማ ከንቲባ አቶ ደስታ አንዳርጌ “ስፖርት የሰው ልጆች ባህል፣ ወግና ማንነት የሚፀባርቅበት ከመሆኑ ባሻገር ለቱሪዝም ዘርፉ ከፍተኛ ሚና ስላለው ለዘርፉ የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ” ብለዋል ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም