በደቡብ ክልል በቀጣዮቹ 15 ቀናት 59 ሺህ ተማሪዎች የልደት ሰርተፊኬት ይወስዳሉ - ኢዜአ አማርኛ
በደቡብ ክልል በቀጣዮቹ 15 ቀናት 59 ሺህ ተማሪዎች የልደት ሰርተፊኬት ይወስዳሉ
ሐዋሳ ነሐሴ 2/ 2011 በደቡብ ክልል በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታት ከ59 ሺህ በላይ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ተማሪዎች የልደት ሰርተፊኬት ምዝገባ እንደሚያከናውኑ ተገለጸ፡፡ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ቀን በክልል ደረጃ ከነሐሴ 7 እስከ 24/ 2011 ባለው ጊዜ ውስጥ በተመረጡ ዞኖች በተለያዩ ዝግጅቶች ይካሄዳል ። የክልሉ ወሳኝ ኩነቶች ኤጄንሲ ስራ አስኪያጅ አቶ ደምስስ ገብሬ ዝግጅቱን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ በየዓመቱ ነሐሴ 4 በአገርና በአፍሪካ ደረጃ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ቀን ይከበራል፡፡ በክልል ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከበረው በዓል በክልሉ በተመረጡ 8 ዞኖች ውስጥ ባሉ 81 የከተማ ቀበሌዎች በዘመቻ መልክ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ይከናወናል፡፡ በዚህም ተማሪዎቹ የልደት ምዝገባ አካሂደው ሰርተፊኬት ይወስዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡ ቁጥሩ ዝቅተኛው እቅድ ነው ያሉት ስራ አስኪያጁ ፣እስከ 100 ሺህ ሊደርስ እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡ እንደ ክልል ከ2008 ጀምሮየወሳኝኩነትምዝገባመጀመሩንአስታውሰዋል። ምዝገባው ከዓመት ዓመት መሻሻል ቢያሳይም፣ በተፈለገው ልክ ውጤት እንዳልተመዘገበበት ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል ፡፡ የምዝገባ ማዕከላቱ ወደ ኅብረተሰቡ አለመውረዳቸው፣የግንዛቤ እጥረትና ለዘርፉ የተሰጠው ትኩረት አናሳነት ዋና ዋናዎቹ ተግዳሮቶች እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ቀኑንምክንያትበማድረግበሚደረገውየንቅናቄመድረክከምዝገባባሻገር፤በተለያዩዘዴዎችግንዛቤየመፍጠርናባለድርሻአካላትንያሳተፈውይይትበማካሄድእጥረቱን ለማቃለል ይሰራል ብለዋል፡፡ በዓሉን በተሳካ መልኩ ለማከናወንም በክልል ደረጃ ዓቢይ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን፣ ክልል አቀፍ መድረክ በሃዋሳ ከተማ እንደሚኖር አቶ ደመስስ ገልጸዋል፡፡ ከወሳኝ ኩነቶች አንዱ የሆነው የልደት ምዝገባ ህጻኑ በተወለደ 90 ቀናት የሚፈጸም ቢሆንም፣ በአዋጁ አንቀጽ አንቀጽ 67/4 መሰረት በተለያዩ ምክንያቶች ያልተመዘቡ ካለፈ በኋላም ቢሆን እንዲመዘገቡ ይደነግጋል ያሉት የኤጄንሲው ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ አጋፋሪ ናቸው፡፡ በመሆኑም በንቅናቄው ለመመዝገብ የተያዘው እቅድ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ተማሪዎችን ያካተተ ሲሆን፣ በቀን በአማካይ የ48 ተማሪዎች ምዝገባ ይከናወናል። ለምዝገባው ስኬት ከክልል ትምህርት ቢሮ ጀምሮ እስከ ታችኛው የትምህርት መዋቅር በቅንጅት በመሰራት ላይ እንደሚገኝ የተናገሩት አቶ ተስፋዬ፣ ተማሪዎች ለትምህርት ምዝገባ ሲመጡ የልደት ሰርተፊኬታቸውን እንዲይዙ ይደረጋል በማለት ተናግረዋል፡፡ ስራውን ለማከናወን የሚያስችሉ ግብዓቶች ወደ የአካባቢው እየተጓጓዙ መሆኑን የገለጹት ምክትል ስራ አስኪያጁ በንቅናቄው ወቅት በሚከናወን ምዝገባ ከክፍያ ነጻ ሰርተፊኬት ይሰጣል ብለዋል፡፡ ከምዝገባው ጎን ለጎንም በኅብረተሰቡና አመራሩ ዘንድ ያለውን ግንዛቤ እጥረት የሚያስተካከሉ ተግባራት እንደሚከናወኑ ገልጸዋል፡፡ "የልደት ምዝገባ ለሁሉም!" የአገር አቀፉ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ቀን መሪ ቃል ነው ተብሏል ።