በአገሪቷ የሚከሰቱ ግጭቶች ዘላቂ መፍትሄ ያሻቸዋል- የኃይማኖት አባቶች - ኢዜአ አማርኛ
በአገሪቷ የሚከሰቱ ግጭቶች ዘላቂ መፍትሄ ያሻቸዋል- የኃይማኖት አባቶች
አዲስ አበባ ኢዜአ ነሃሴ 2 2011 በአገሪቷ የተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ግጭቶችን ዘላቂ መፍትሄ በማበጀት መፍታት እንደሚገባ የኃይማኖት አባቶች አሳሰቡ። ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተወካይ አባ ገብረሃና ገብረ ጻዲቅ ቤተክርስቲያን ከመቸውም ጊዜ በላይ ለአገር አንድነትና የሰላም ግንባታ እየሰራች ነው። ቀደም ሲል የነበሩ የመቻቻልና አብሮ የመኖር እሴቶች እየተሸረሸሩ መምጣታቸውን ጠቅሰው ወደ ቀድሞ ነባራዊ ሁኔታው ለመመለስ መስራት ይገባል ነው ያሉት። አሁን ላይ በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች የሚከሰቱ ግጭቶችን በማጤን ዘላቂ መፍትሄ በማበጀት መፍታት ይገባልም ብለዋል። የኃይማኖት ተቋማት የጋራ የሆነችውን አገር ሰላምና መረጋጋት ለማስጠበቅ በጋራ የመስራት ሃላፊነት እንዳለባቸውም ጠቁመዋል። የመንግስትም አገር የመምራት ሃላፊነት ምቹ የኢኮኖሚና ፖለቲካ ሂደት እንዲሁም የህግ የበላይነት በማስፈን ግደታውን መወጣት ይኖርበታል ብለዋል። ይህንን አገራዊ ግደታ ለመወጣት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እስከታች ድርስ መዋቅር ዘርግታ እየሰራች መሆኑንም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስ የልጆችና የወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ሃላፊ መምህር ጸጋሁን አሰፋ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብዙም ባልተለመደ መልኩ በተለያዩ አካባቢዎች ማፈናቀልና ግጭቾች በስፋት መስተዋሉ ሁሉንም አሳስቧል ብለዋል። በመሆኑም ችግሩን ለመፍታት መንግስት፣ የኃይማኖት ተቋማትና ህብረተሰቡ ዘላቂ መፍትሄ ለመሻት በጋራ መስራት አለባቸው ብለዋል። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብጹእ ካርዲናል ብርሐነ እየሱስ ሱራፌል እንደገለጹትም አልፎ አልፎ የሚስተዋለውን የፀጥታ መደፍረስ ለመፍታት በመደማመጥ በመደጋገፍና በመመካከር ማስወገድ ይገባል። በአሁኑ ወቅት ለአገሪቷ ከሁሉም በላይ መቻቻል አስፈላጊ በመሆኑ ትኩረት ልንሰጠው ይገባልም ነው ያሉት። መንግስትሰላምንለማምጣትየጀመረውየህዝቦችንቅርርብየሚያመጣየእርቀ ሰላምኮሚሽንአቋቁሞመስራቱመልካምጅምርመሆኑንምጠቅሰዋል። የሰላም ሚኒስቴር የሃይማኖትና የእምነት ጉዳዮች ሰላምና የመከባበር ማስፈን ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ዱቤ በበኩላቸው በአገሪቷ የለላም እሴቶችን ለማጎልበት የሃይማኖት አባቶች ሚና ወሳኝ ነው ብለዋል። በመሆኑምአገሪቷየጀመረችውንየሰላም፣የልማትእንዲሁም አብሮየመኖርእሴትለማጠናከርመንግስትከኃይማኖት ተቋማት ጋርአብሮእንደሚሰራአረጋግጠዋል። በኢትዮጵያየአረብኤምሬትስኤምባሲአዘጋጅነት‘የመቻቻልዓመት”በሚልመሪሃሳብየሰላምሚኒስቴርናየተለያዩ የኃይማኖትተቋማትመሪዎችበጋራመክረዋል።