ቡና በመላክ ከፍተኛ ገቢ ያስገኙ ላኪዎች ሸልማት ተበረከተላቸው

153
አዲስ አበባ ኢዜአ ሀምሌ 28/2011 የቡና ምርትን በጥራት አዘጋጅተው ወደ ውጭ በመላክና በተለያዩ የቡና ንግድ ዘርፍ ከፍተኛ ገቢ ያስገኙ 60 ቡና ላኪዎች ዛሬ ተሸለሙ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ጋር በመሆን ትናንት የተጀመረው የውይይትና የእውቅና መድረክ ዛሬም ቀጥሏል። በዛሬው ዕለት 60 ለሚሆኑ የቡና ላኪዎች የእውቅናና ሽልማት ስነስርአት ተካሂዷል። በዚህም የቡና ምርትን በጥራት አዘጋጀተዉ ወደውጪ በመላክ ከፍተኛ ገቢ ያስገኙ አርሶ አደሮችና ሴት ባለ ሃብቶች ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል። የቡና ምርትን እሴት በመጨመር ወደ ውጪ በመላክ ከፍተኛ ገቢ ያስገኙም ተሸላሚ ሆነዋል። ቀርጫንሺ ትሬዲግ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ትራኮን ትሬዲግ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግልማህበር እና አደም ከድር ሐጂ ሀሰን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ተሸልመዋል። ከሽልማቱ ስነ ስርአት በኋላ የግብርና ሚኒስትር ኡመር ሐሰንን ጨምሮ በፕሮግራሙ ላይ የተሳተፉ በቢሺፍቱ ችግኝ ተክለዋል።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም