የኢንዱንዥያና የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎችን በማስተሳሰር የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲያደርጉ እየደገፉ መሆናቸውን አምባሳደር አልቡሽራ አስታወቁ - ኢዜአ አማርኛ
የኢንዱንዥያና የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎችን በማስተሳሰር የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲያደርጉ እየደገፉ መሆናቸውን አምባሳደር አልቡሽራ አስታወቁ
ሐምሌ 26/20111 የኢንዱንዥያ ዩኒቨርሲቲዎችን ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር በማስተሳሰር የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲያደርጉ በመደገፍ እየሰሩ መሆናቸውን በኢትዮጵያ የሀገሪቱ አምባሳደር ሚስተር አልቡሽራ ባስኑር አስታወቁ። አምባሳደሩ ትናንት የወሎ ዩኒቨርሲቲንና የአይጠየፍ ቤተ መንግስትን በመጎብኘት የችግኝ ተከላ አካሄደዋል፡፡ ከጉብኝታቸው በኋላ እንደገለጹት የኢትዮጵያን ዩኒቨርሲቲዎች ከኢንዱንዥያ አቻዎቻቸው ጋር በማስተሳሳር የልምድ ልውውጥና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲያደርጉ እየሰሩ ናቸው። በኢንዱንዥያ ከ600 በላይ የመንግስትና የግል ዩኒቨርሲቲዎች እንዳሉ ያመለከቱት አምባሳደሩ “ዘመናዊ ቴክኖሎጂና የፈጠራ ሥራዎችን የሚያጎለብቱ ቤተ ሙከራዎች አሉ “ብለዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ዩንቨርሲቲዎች ጋር በማገናኘት መምህራንና ተማሪዎች የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉና የፈጠራ ሥራዎችን እንዲያጎለብቱ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ እንደ አምባሳንደሩ ገለጻ እስካሁን ከባህርዳርና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ቁርኝትፈጥረዋል፤ ከ15 በላይ ተማሪዎች ወደ ኢንዱንዥያ ሂደው የልምድ ለውውጥ እያደረጉ ነው። “በቀጣይ ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር ለማስተሳሰርም ከተቋሙ አመራሮች ጋር ስምምነት ፈጥረናል፤ የኢንዱንዥያ ተማሪዎችም ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ “ብለዋል፡፡ ምሩቃን ተማሪዎችንም ከኢንዱስትሪና ፋብሪካዎች ጋር በማስተሳሰር ሥራ አጥነትን ለመቀነስ በጋራ ለመስራት ፍላጎትእንዳላቸውም አምባሳደሩ አመልክተዋል፡፡ የወሎ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር መንገሻ አየነ በበኩላቸው ከኢንዶንዥያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር ለመተሳሰር ያደረጉት ስምምነት አዳዲስ ቴክኖሎjiዎችን ለመጠቀምና lተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች ምቹ ሁኔታ እንደመፈጠር ተናግረዋል። “ተማሪዎች የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ የመውቂያና ማጨጃ ማሽን፣ ኬሚካል መርጫ፣ የመኖ ማቀነባበሪያና ሌሎች ዘመናዊ ማሽኖችንም በፈጠራ ሥራቸው አከናውነው ሙከራ ላይ ናቸው” ብለዋል። የተፈጠረውን ግንኘነት በማጠናከር ጅምሮችን ለማሳደግም ከኢንዶንዥያ ጋር እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡ አምባሳደር ሚስተር አልቡሽራ ባስኑር በአካባቢው በተደረገላቸው መስተንግዶና አቀባባል መደሰታቸውን ተናገረው በቆይታቸውም የመጡበትን ተልኮ ማሳካታቸውንም ገልጸዋል። የሁለት ቀናት ቆይታቸውን አጠናቀውም ዛሬ ሲመለሱ አሸኛኘት ተደርገላቸዋል፡፡