ቀጥታ፡

የዳያስፖራዎች ፌስቲቫል ማምሻውን በመቀሌ ከተማ ተጀመረ

መቐለ ኢዜአ ሐምሌ 24 /2011 አለም አቀፍ የትግራይ ክልል ተወላጅ ዳያስፖራዎች ፌስቲቫል ዛሬ ማምሻው በመቀሌ ከተማ ተጀመረ። ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋጀው የዲያስፖራዎች ፌስቲቫል በተለያዩ አለማት የሚገኙና ከሁለት ሺህ በላይ የሚሆኑ የክልሉ ተወላጆች ተሳታፊዎች መሆናቸው የክልሉ ዳያስፖራ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍስሃዬ አለማየሁ ገልጸዋል። ለሰባት ቀናት በሚቆየው ፌስቲቫሉ የክልሉ ልማት በማፋጠን ዲያስፖራዎች ስለሚኖራቸው ሚና ውይይት እንደሚካሄድ  አስረድተዋል። በፌስቲቫሉ መክፈቻ ስነስርዓት  የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዳይሬክተር፣  የመቀሌ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ተገኝተዋል። ከዚህ ቀደም ብሎ የክልሉን የልማት እንቅስቃሴ ከየት ወዴት ፣  የኢንቨስትመን እንዲሁም የልማት ተቋማት እንቅስቃሴዎች የሚያሳይ የምርትና አገልግሎት አውደ ርዕይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ተከፍቶ በዳያስፖራቹ ጉብኝት ተደርጓል፡፡ በአውደ ርዕዩ  150 የሚሆኑ ተቋማት ምርትና አገልግሎታቸውን ማቅረባቸው የዝግጅቱ አስተባባሪ አቶ ሐጎስ ወልደኪዳን አስታውቀዋል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም