የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 6ኛ አመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔውን ከሐምሌ 25 እስከ 27 ቀን 2011 ዓ.ም ያካሄዳል

59
አዲስ አበባ ኢዜአ ሀምሌ 23/2019  የአዲስ አበባ ከተማ  አስተዳደር ምክር  ቤት 6ኛ አመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ የበጀት ዓመቱን የማጠቃለያ ጉባኤውን ከሐምሌ 25 እስከ 27 ቀን 2011 ዓ.ም ያሳውቃል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ የ2011 ዓ.ም የማጠቃለያ ጉባኤ ከሐምሌ 25 እስከ 27 ቀን 2011 ዓ.ም ያካሄዳል። ምክር ቤቱ በጉባኤው ላይ የምክር ቤቱን  መደበኛ ቃለ ጉባኤ ያፀድቃል፤ የምክር ቤቱን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በማንሳትም ይወያያል። በተጨማሪም  የከተማ አስተዳደሩን የ2011 በጀት አመት የስራ አፈፃፀም  ይገመግማል፤ የአስተዳደሩ ዋና ኦዲት ና ፍርድ ቤትም  የአፈፃፀም  ሪፖርታቸውን  አቅርበው በማወያየት የሚያፀድቁበት እንደሆነም  የምክር ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር  አቶ አዲስ አለም እንቻላቸው ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቀዋል። የአስተዳደሩ 2012 የበጀት አመት በጀት የሚፀድቅበትና ምክር ቤቱ የተለያዩ ሹመቶችን  የሚያፀድቅበት እንደሚሆንም ይጠበቃል። ምክር ቤቱ በበጀት ዓመቱ በቁጥጥርና ክትትል ስራው ላይ  የተሻለ ስራ መስራቱም ተገልጿል።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም