ቀጥታ፡

በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሚመራ የልኡካን ቡድን በምዕራብ ጎንደር ዞን ጉብኝት እያካሄደ ነው

ጎንደር ኢዜአ ሐምሌ 23/ 2011ዓ.ም- በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የሚመራ የልኡካን ቡድን በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውሃ ከተማ የሚገኘውን የኢንዱስትሪ መንደር እየጎበኘ ነው። ከኢንዱስትሪ መንደሩ በተጨማሪ የልዑካን ቡድኑ በአካባቢው ባለሃብቶች እየተከናወነ ያለውን የሰሊጥ ልማት ይጎበኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከጉብኝቱ በኋላም በኢንዱስትሪ መንደሩ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ከተሰማሩ የሃገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች እንዲሁም ሠራተኞቻቸው ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በጉብኝቱ የኢትዮ-ቴሌኮምና የኢትዮጵያ ኤለክትሪክ ኃይል ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነርና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም