ቀጥታ፡

ጅቡቲ የነበሩ 361 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ ሰኔ 5/2010 በጅቡቲ በስደት ላይ የነበሩ 361 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መግባታቸውን  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ስደተኞቹ ወደ አገራቸው የተመለሱት በጅቡቲ ያለው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ከአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ጋር ባደረገው ጥረት መሆኑን ሚኒስቴሩ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ አስታውቋል። ስደተኞቹ ወደ አረብ አገራት ለመሄድ በህገ-ወጥ መንገድ በስደት ላይ የነበሩና የመን ውስጥ ባለው ጦርነት ምክንያት ጅቡቲ የተመለሱ ናቸው ተብሏል። በነገው እለትም 24 ስደተኞች ወደ አገራቸው ይገባሉ ተብሏል።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም