በሶማሌ ክልል ከ423 ሺህ በላይ ችግኞች ተተከሉ - ኢዜአ አማርኛ
በሶማሌ ክልል ከ423 ሺህ በላይ ችግኞች ተተከሉ
ሐምሌ 22 ቀን 2011 (ኢዜአ )በሶማሌ ክልል በአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ ቀን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በተገኙበት የተጀመረው የችግኝ ተከላ ፕሮግራም እንደቀጠለ ነው። እስከ እኩለ ቀን ድረስ በነበረው ጊዜ ውስጥ 423 ሺህ 692 ችግኞች መትከል እንደተቻለ የክልሉ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ኢማን ገልፀዋል ። የችግኝ ተከላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስተፌ መሐመድን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። አሁንም በቀጠለው የችግኝ ተከላው ስራ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮችና አባላት፣የክልሉ የፀጥታ ሀይል ኃይሎች ፣ የክልል አመራሮችና የመንግስት ሰራተኞች ጭምር እየተሳተፉ ነው ። በሀገር ደረጃ በአንድ ቀን 200ሚሊዮን ችግኝ በመትከል በአለም አቀፍ ደረጃ ሪከርድ ለማስመዝገብ ነው ዛሬ ከጥዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ስራው ቀጥሎ ያለው።