"ችግኝ የህልውና ጉዳይ ነው፤ የእምነት፤ የባህል የኢኮኖሚ፤ ዛፍ ማለት እኛ ነን" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ - ኢዜአ አማርኛ
"ችግኝ የህልውና ጉዳይ ነው፤ የእምነት፤ የባህል የኢኮኖሚ፤ ዛፍ ማለት እኛ ነን" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
አዲሰ አበባ ኢዜአ ሀምሌ 19/2011"የዛፎች ጉዳይ ለእኛ የውበት ጉዳይ ብቻ አይደለም፡፡ የህልውና ጉዳይ ነው፤ የእምነት ጉዳይ ነው፤ የባህል ጉዳይ ነው፤ የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው፤ ዛፍ ማለት እኛ ነን- እኛ ማለት ያለዛፍ ምንም ነን"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ሐምሌ 22 ቀን የሚደረገዉን ብሔራዊ የችግኝ ተከላ ቀን በተመለከተ ባስተላለፉት መልዕክት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በደንና በእንስሳት የተሞላች እንደነበረች ለብዙ ዘመናት ሲሰሙ የነበሩ የሙዚቃ ዜማዎችና ተረቶች በምስርክርነት ጠቅሰዋል። "እኛ ግን አባቶቻችን ያቆዩልንን አገር ልምላሜዋንና አረንጓዴ ውበቷን ከትዝታ ብቻ አወዳጅተን አደራችንን በልተናል" ብለዋል በመግለጫቸው፡፡ በዚህም የበረሃማነት መስፋፋትና የአየር ንብረት መዛባት ያስከተለው ቀውስ አገራችንን አደጋ ላይ ከመጣል አልፎ የስሟ መገለጫ እስከመሆን መድረሱን አስታውሰዋል። ላለፉት 40 ዓመታት ብቻ ኢትዮጵያን በሚመታት ድርቅ በምግብ ዋስትና የተፈተነችው፣ ወገኖቻችንን ከክብር ማማ ወርደው የተረጂነት ወለል ላይ የተቀመጡት፣ ወንዞች የጎደሉት፣ ምንጮች የነጠፉት፣ ወይና ደጋው በርሃ፣ ደጋው ቆላ እየሆነ መምጣቱን ገልጸው የደን መራቆት የህልው አደጋ መንስኤ መሆኑን አንስተዋል። ከተሞች ከኢንዱስትሪ ከተሽከርካሪ ጢስ ብክለት ባሻገር፣ የሶሰት ፀሀይ ያህል ንዳድ ሆነው የሚያቃጥሉት ከዛፎች በመራቆታቸው መሆኑን ጠቅሰው፤ "ከተሞች መኖሪያ እንዲሆኑ ደናማ መሆን አለባቸው" ነው ያሉት። "የዛፎች ጉዳይ ለእኛ የውበት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው፤ ካለዛፍ ምንም ነን" ያሉት ጠቅላይ ሚኒሰትሩ፤ "ዛፍ ማለት እኛ ነን፤ የዛፎች ጉዳይ የእምነት፤ የባህል፤ የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው" ብለዋል። "ይህች አገር ከአባቶቻችን የወረስናት ብቻ ሳትሆን ከልጆቻችንም የተዋስናት መሆኗንም ማሰብ ተገቢ ነው" ብለዋል። "ከልጆቻችን ነፍስ ላይ የነጠቅነውን በምቹ አገር የመኖር የህልውና መሰረት ሳንውል ሳናድር ከመመለስ እና ከመተካት የሞራል፣ የእምነት እና የሰብአዊነት ጽኑ ጥያቄ ጋር የተፋጠጥንበት ወቅት ላይ ደርሰናል" ብለዋል። በዚህም "የአገራችንን የደን ሽፋን እንዲያገግም ማድረግ ህልውናችንን ማጽናት፣ እምነታችንን መጠበቅ፣ ባህላችንን ማበልጸግ፣ ኢኮኖሚያችንን ማዳበር ነው" ሲሉ መልክት አስተላልፈዋል። "በመጭው ሰኞ ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም በሚደረገው ብሔራዊ የችግኝ ተከላ ቀን 200 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ቀን በመትከል የያዝነው ክረምት ከማለፉ በፊትም አራት ቢሊዮን ችግኞችን ተክለን ግባችንን እንመታለን" ብለዋል። "ለአንድ አገር ጉዳይ፣ አንድ ሆነን በዓላማ ከተነሣን የሚሳነን ነገር እንደማይኖር የአረንጓዴ አሻራ ስኬታችን ምስክር መሆኑን ነው" ሲሉም አብራርተዋል። በመሆኑም "ሐምሌ 22 ቀን ሁላችንም ማልደን በመውጣት፣ ችግኞችንም በተገቢ መንገድ በመትከል፣ አረንጓዴ አሻራችንን እናሳርፍ፡፡ ነገንም ዛሬ እንትከል" ሲሉ ጥሩ አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም የሚደረገዉን ብሔራዊ የችግኝ ተከላ ቀን በተመለከተ ያስተላለፉት መልእክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡- ለብዙ ዘመናት ከኢትዮጵያ ሰማይ ስር ሲስተጋባ የኖረውና ‹ለምለሟ ሀገሬ› የሚለው እድሜ ጠገብ ዜማ የልጆቻቸን የዛሬ እውነታ የእኛ ደግሞ ከጆሯችን ሁሌም ያለ ቅርብ ትዝታ ነው፡፡ ትላንት እውነት እና ሀሴት የነበረው፤ ዛሬ ግን ምኩን እና ቁጭት ሆኖ የቀረው ዝማሬ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ኅሊና ውስጥ አብዝቶ ይመላለሳል፡፡ እውነት ነው ሀገራችን ለምለም ነበረች- ዛሬ ግን አይደለችም፤ ምክንያቱም አባቶቻችን ያቆዩልንን እኛም በተራችን ለልጀቻችን አላቆየንም- እናም ልምላሜዋን እና አረንጓዴ ውበቷን ከትዝታ ብቻ አወዳጅተን አደራችንን በልተናል፡፡ ዜማዎቻችን ብቻ ሳይሆኑ ተረቶቻችንም ሀገራችን በደን የተሞላች እንደነበረች ይነግሩናል፡፡ በተረቶቻችን ውስጥ የምናገኛቸውን ብዙዎቹን እንስሳት ዛሬ በአካባቢያችን አናገኛቸውም፡፡ በየቋንቋችን ስማቸው ብቻ የቀረው የዛፍ ዓይነቶች ሀገራችን ዓይነተ ብዙ ደን እንደነበራት ቋሚ ምስክሮች ናቸው፡፡ የዛፎችጉዳይለእኛየውበትጉዳይብቻአይደለም፡፡የህልውናጉዳይነው፤የእምነትጉዳይነው፤የባህልጉዳይነው፤የኢኮኖሚጉዳይነው፤ዛፍማለትእኛነን- እኛማለትያለዛፍምንምነን፡፡የበረሃማነትመስፋፋትናየአየርንብረትመዛባትያስከተለውቀውስሀገራችንንአደጋላይከመጣልአልፎየስሟመገለጫእስከመሆንደርሷል፡፡ባለፉትዐርባዓመታትብቻእያሠለሰየሚመታንድርቅበምግብእህልራሳችንንለመቻልየምናደርገውንትግልተፈታትኖታል፤ወገኖቻችንንምከክብርማማአውርዶየተረጅነትወለልላይአስቀምጦብናል፡፡የዝናብወቅቶቻችንእየተዛቡ፣ለጎረቤትይተርፉየነበሩትወንዞቻችንእየጎደሉ፤ምንጮቻችንእየነጠፉ፤ወይናደጋውበረሐ፣ደጋውቆላእየሆነየህልውናአደጋጋርጦብናል፡፡ያራሳችንንህልውናበራሳችንጥርስግጠነው- የነበረውንአፍርሰንእንዲያያልነበርንመስለናል፡፡ከተሞቻችንበአንድበኩልበኢንዱስትሪዎችናበተሸከርካሪዎችጢስይበከላሉ፤በሌላበኩልደግሞዛፎቻቸውንጨርሰውከአንድፀሐይቢሆኑምየሦስትፀሐይያህልበገረረንዳድተንቀልቅለውህያውበድኑንያቃጥላሉ፡፡ከተሞቻችንየከተማመቃጠያመሆናቸውቀርቶየከተማመኖሪያእንዲሆኑደናማከተሞችመሆንአለባቸው፡፡ ወገባችንንአሥረንየምንሠራቸውግድቦችበደለልእየተሞሉናበውኃእጥረትእየተመቱልፋታችንንመናእያስቀረነውነው፡፡እጃችንንበእጃችንእየበላንጸጸትቁጭታችንብዙነው፡፡ይህቁጭትእናመብሰክሰካችንየይቸላልስሜታችንንአቀጣጥሎወደአረንጓዴሰገነታችንበሀይልካንደረደረንእሰየው፤ቁጭትብቻከሆነግንዋይታችንንየማይቋጭያውከንቱቁትብቻነው፡፡ሐይቆቻችንየነበራቸውንቦታእየለቀቁ፣አንዳንዶቹከነባርይዞታቸውሲሸሹሌሎቹጨርሰውእየደረቁነው፡፡ሀዘናችንመሪርሆኗል፡፡ለነሀረማያያፈሰስነውእንባገናከጉንጫችንሳይደርቅየሌሎችሀይቅጅረቶቻችንምህልውናጉዳይምለሌላሀዘንእያጨንነጋችንንጽልምአርጎታል፡፡በዚህምየተነሣበዓሣሀብታችንላይፈተናእየተደቀነነው፡፡በሐይቆቻችንላይሠፍረውይኖሩየነበሩትአዕዋፍሀገርጥለውእየኮበለሉበሐይቆችውስጥየሚኖሩእንስሳትምዘራቸውእየተመናመነነው፡፡እንባችንንከአይነችንለመክላትእናዋይታችንንወደዝማሬለመቀየርማንይምጣ? ለእኛህመምእናስቃይማሻርያውእናፈውሱምያለውእኛውእጅነው፡፡ዓለምያደነቃቸውታላላቅቤተእምነቶቻችየተሠሩትከሀገርበቀልዛፎችበተገኙእንጨቶችነበር፡፡በውስጣቸውየምናገኛቸውቅርሶችናንዋያተቅዱሳትየተዘጋጁትከኢትዮጵያውያንእንጨቶችነበር፡፡ሥዕሎቻችን፣ቅርጾቻችንናየወግዕቃዎቻችንበሙሉየደኖቻችንውጤቶችነበሩ፡፡ቀደምቶቻችንየተጠበቡባቸውዓምዶችናወጋግራዎች፣በሮችናመስኮቶች፣ጣራዎችናአቴናዎችየደኖቻችንትሩፋቶችነበሩ፡፡ትውፊታዊክዋኔዎቻችንደኖቻችንንአበክረውይፈልጓቸዋል፡፡አረንጓዴውአለማችንየሁለነገራችንአልፋእናኦሜጋነው፡፡ሰርግሀዘናችን- ስግደትሶላታችን- ልደትሞታችን- አምልኮከበራችንወግእናጫወታችንእንኳንከዛፍ- ደኖቻችንጋርእጅጉንተሰናስሏል፡፡ህይወታችንከደኖቻችንጋርየተያያዘነው፡፡የደኖቻችንመመናመንበጎዕሴቶቻችንእንዲመናመኑአድርጎብናል፡፡ዕርቅ፣ሸንጎ፣ውይይት፣ታሪክነገራ፣በባህላችንውስጥየሚከወኑትበዋርካዎቻችንሥርነው፡፡በሁሉምኢትዮጵያዊልብእናህውስታውስጥአረንጓዴደኖቻችንየደግነት፣የፍቅር፣የሰላም፣የህይወትእናየተስፋውካዮችናቸው፡፡በገጠሬውሕይወትናበከተሜውትዝታውስጥየሚገኙትየዱርፍሬዎችየባህላችንአካላትነበሩ፡፡ሌላውቀርቶባህላዊየሙዚቃመሣሪያዎቻችንእንኳንየሚዘጋጁትከደንውጤቶቻችንነው፡፡በባህላችንየአንድዋርካመውደቅየአንድእንጨትመውደቅሳይሆንየአንድትልቅሰው፤የአንድትልቅሽማግሌመውደቅምልክትነው፡፡በሀገራችንብዙወገኖቻችንኑሯቸውንበደኖችናበደንውጤቶችላይየተመሠረተነው፡፡የደንፍሬዎችንለቅመው፣የደንቅጠሎችንሰብስበው፣የደንውጤቶችንቆርጠው፣የደንውጤቶችንወደልዩልዩዕቃዎችቀይረው፣በመሸጥኑሯቸውንየመሠረቱናቸው፡፡የሀገሪቱዋነኛየውጭምንዛሪምንጮችበአንድምበሌላምመንገድከደንውጤቶቻችንጋርየተያያዙናቸው፡፡ደኖቻችንናየዱርእንስሶቻችንየቱሪዝምገቢያችንመሠረቶች፣የአይናችንማረፍያጌጦች፣የባህል- ወግእናእምነታችንምመከሰቻናቸው፡፡እነዚህንሁሉስንመለከትነውየዛፍጉዳይለእኛየቅንጦትጉዳይየማይሆነው፡፡ከዚህበፊትምእንደምለውይህችሀገርከአባቶቻችንየወረስናትብቻሳትሆንከልጆቻችንምየተዋስናትመሆኗንምማሰብተገቢነው፡፡ እኛም በተራችን ለልጆቻችን ስናስረከባት ከነበረሀዋ፣ ከነንዳዷ፣ ከነ ድርቋ እና ከነደለሏ እንዳይሆን የቤት ስራችንን እንሰራ ዘንድ ይገባናል፡፡ ከልጆቻችን ነፍስ ላይ የነጠቅነውን በምቹ ሀገር የመኖር የህልውና መሰረት ሳንውል ሳናድር ከመመለስ እና ከመተካት የሞራል፣ የእምነት እና የሰብአዊነት ጽኑ ጥያቄ ጋር የተፋጠጥንበት ወቅት ላይ ደርሰናል፡፡ የሀገራችንን የደን ሽፋን እንዲያገግም ማድረግ ህልውናችንን ማጽናት፣ እምነታችንን መጠበቅ፣ ባህላችንን ማበልጸግ፣ ኢኮኖሚያችንን ማዳበር ነው፡፡ አራት ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ስንነሣ ለህልውናችን፣ ለእምነታችን፣ ለባህላችንና ለኢኮኖሚያችን ስንል ታጥቀን መነሣታችንም ጭምር ነው፡፡ ሕዝቡ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ምዕራብ ያሳየው ተነሣሽነት ይህን ዓላማ እንደተረዳው የሚያሳይ ነው፡፡ ይህንን ሀገራዊ ዓላማ ለማሳካት እስካሁን ባደረግነው አረንጓዴ አሻራን የማሳረፍ ርብርብ ቢልዮኖች ችግኞችን ተክለናል፡፡ ሰኞ ሐምሌ 22 ቀን በምናደርገው ብሔራዊ የችግኝ ተከላ ቀን 200 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ቀን በመትከል የዓለምን ክብረ ወሰን እንሰብረዋለን፡፡ የያዝነው ክረምት ከማለፉ በፊትም አራት ቢሊዮን ችግኞችን ተክለን ግባችንን እንመታለን፡፡ ይህን ስኬት ለማምጣት የሚኒስቴር መ/ቤቶችና የክልል አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ በችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች የሚገኙ ሠራተኞች፣ የግብርና ባለሞያዎችና ምሁራን፣ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች፣ ኮሜዲያን፣ የሚዲያ ኃላፊዎችና ጋዜጠኞች፣ ነጋዴዎችና ታላላቅ ኮርፖሬሽኖች፣ ወጣቶችና ሕጻናት፣ አጓጓዦችና የጉልበት ሠራተኞች ላደረጉት ምትክ የማይገኝለት አስተዋጽዖ በራሴና በኢፌዲሪ መንግሥት ስም ላመሰግን እወዳለሁ፡፡ ለአንድ አገር ጉዳይ፣ አንድ ሆነን በዓላማ ከተነሣን የሚሳነን ነገር እንደማይኖር የአረንጓዴ አሻራ ስኬታችን ምስክር ነው፡፡ ከደን የተራቆተችውን ሀገራችንን ለማልበስ እንደተነሣነው ሁሉ ከሰላም ከፍቅርና ከይቅርታ እየተራቆተች የመጣችውን ሀገራችንንም አንድ ሆነን ማልበስ አለብን፡፡ አራት ቢሊዮን ዛፍ በአንድ ክረምት መትከል ከቻልን አራቱን አስፈላጊ ሀገራዊ ዕሴቶችን፡- ሰላምን፣ ይቅርታን፣ ፍቅርንና አንድነትን መትከልና ማሳደግ አያቅተንም፡፡ በፍጹም፡፡ በቀሪው ጊዜ የተከልናቸውን ችግኞች በመጠበቅ፣ በመንከባከብና ለፍሬ በማብቃት መትከል ብቻ ሳይሆን ማሳደግም እንደምንችል እናሳይ፡፡ ዛፍ ብሔር፣ ቋንቋ፣ እምነትና ርእዮተ ዓለም የለውም፡፡ ሁሉም ዛፍ የሁላችንም ነው፡፡ የሠራነው ሥራም ከእነዚህ ሁሉ በላይ ነው፡፡ ክብካቤና ጥበቃውም እነዚህን ልዩነቶች ሁሉ አልፎ ሊደረግ የሚገባው ነው፡፡ ሐምሌ 22 ቀን ሁላችንም ማልደን በመውጣት፣ ችግኞችንም በተገቢ መንገድ በመትከል፣ አረንጓዴ አሻራችንን እናሳርፍ፡፡ ነገንም ዛሬ እንትከል፡፡ ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራ፣ ተከብራና በልጽጋ ለዘላለም ትኑር! ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ! ሐምሌ 19 ቀን 2011 ዓ.ም