ቀጥታ፡

አቤት ሆስፒታል የዳሌ አጥንት መገጣጠሚያ ንቅለ ተከላ አካሄደ

አዲስ  አበባ  ሀምሌ 18/2011የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ህክምና ኮሌጅ አካል በሆነው አቤት ሆስፒታል የዳሌ አጥንት መገጣጠሚያ ንቅለ ተከላ ተካሄደ። የኢትዮትዮጵያ እና የአሜሪካ ሐኪሞች ቡድን ከአቤት ሆስፒታል ጋር በመተባበር ለሁለት ሳምንት የዳሌ አጥንት መገጣጠሚያ መሸራረፍ ህክምና ሲሰጥ ቆይቷል። ህክምናውን ያገኙ ታካሚዎች በበኩላቸው ከዚህ በፊት በዳሌ አካባቢ የሚሰማቸው ህመም እንደቀነሰላቸው ገልጸዋል። ከአሜሪካየመጡሰባትአባላትንየያዘውናበዶክተር ክብረትከበደየተመራውየህክምናቡድንከአቤትሆስፒታልየህክምናባለሙያዎችጋርበተመባበርከባለፈውሳምንትሰኞጀምሮህክምናውን ሲሰጥቆይቷል። የዳሌ አጥንት መጋጠሚያ መሸራረፍ ስቴሮይድ የሚሰኙ መድሃኒቶችን ለረጅም ጊዜ መውሰድ፣ በዕድሜ እንዲሁም የቲቢ ህመም በሽታ ወደ መገጣጠሚያ በሚገባበት ጊዜ እንዲሁም በአደጋ ጊዜ እንደሚከሰት የህክምና ባለሙያዎቹ ተናግረዋል። የህክምናቡድኑመሪዶክተርክብረትከበደለኢዜአእንዳሉት፤ህክምናው 'ዙመሪባዮሜት'ከሚባልየአጥንትህክምናአገልግሎትበሚሰጥድርጅትናበኢትዮትዮጵያ እና የአሜሪካ ሐኪሞች ቡድንትብብርበአቤትሆስፒታልተካሂዷል። የሐኪሞቹ ቡድን ህክምናየሚሰጥበትንመሳሪያናበሰውነት ውስጥየሚገባውንመሳሪያምጭምርይዞወደ አገርውስጥእንደገባየገለጹትዶክተርክብረት፤እስከ አሁን ድረስ 12 ሰዎችህክምናእንዳገኙተናግረዋል። ''ህክምናውንለማግኘትአንድሰውእስከ 250 ሺህ ብርየሚያስፈልገውሲሆንየህክምናቡድኑለህሙማኑየሰጠውህክምናበነፃነው'' ብለዋል። ይህምአገሪቱንከውጭምንዛሬእንድትድን የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ ታካሚዎችህክምናውንሳይንገላቱ የቤተሰብ ድጋፍን እያገኙበአገራቸውእንዲታከሙያስቻለእንደሆነምአብራርተዋል። ህክምናውበቀጣይተጠናክሮእንዲቀጥልየኢትዮትዮጵያ እና የአሜሪካ ሐኪሞች ቡድን ድጋፍእንደሚያደርግያስረዱትዶክተርክብረትህክምናውበጋራመደረጉኢትዮጵያዊያንሐኪሞችየልምድእንዲቀስሙየሚያስችልመሆኑንጠቁመዋል። በቀጣይ በኢትዮትዮጵያ እና የአሜሪካ ሐኪሞች ቡድን እየተገነባ ያለው ሆስፒታል ሲጠናቀቅ ህክምናውን ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ለመስጠት ዕቅድ እንዳለም ዶክተር ክብረት አመልክተዋል። በህክምናው የተሳተፉ የአቤት ሆስፒታል ሐኪሞች በበኩላቸው ለሁለት ሳምንት ያህል በዘለቀው ህክምና ወረፋ ሲጠብቁ የቆዩ ህሙማን አገልግሎቱን እንዲያገኙ ማስቻሉን ገልጸዋል። የህክምና ባለሙያዎቹ በቀጣይ ስራውን በአገር ውስጥ ባለሙያዎች ለማከናወን የሚያስችል አቅም መገንባታቸውንና መሳሪያዎቹ ሲሟሉ ህክምናውን ለመጀመር ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። ዶክተርኢብራሂምአህመድበህክምናው የተሳተፉ ነርሶችና ከቡድኑ ጋር የመጡ የህክምና ተማሪዎችም በበኩላቸው በህክምናው መሳተፋቸው እውቀት እንዲያገኙ ያስቻላቸው መሆኑን ገልጸዋል። ታካሚዎች በበኩላቸው በህመሙ ሲሰቃዩ መቆየታቸውንና ህክምናውን ካገኙ አጭር ጊዜ ቢሆንም ለውጥ እንዳለው ተናግረዋል። ህመሙ ከጀመራቸው ሁለት ዓመት እንደሆናቸውና በህመሙ ሳቢያ መንቀሳቀስ ስላልቻሉ ስራ ፈተው እንደነበር የገለጹት አቶ ጃምቦ ተፈራ በእነዚህ ዓመታት ከማስታገሻ በስተቀር ያገኙት ህክምና እንዳልነበር ተናግረዋል። ሌላዋ ታካሚ ወይዘሮ ሙሉብርሃን ወልደገብርኤል በበኩላቸው ከስድስት ዓመት ወዲህ በመውደቃቸው ለህመሙ መጋለጣቸውን ገልጸው አሁን ያገኙት ህክምና የተሻለ ተስፋ እንደሰጣቸው አስረድተዋል። ታካሚዎቹ ህክምናውን ለሰጧቸው የአቤት ሆስፒታልና የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ሐኪሞች ቡድን ምስጋና አቅርበዋል። ህክምናውእስከ ነገ ሐምሌ 19 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስየሚቆይ ሲሆን 18 ያህልሰዎችንለማከምየህክምናቡድኑአቅዷል። ህክምናውን ለማግኘት 300 ህሙማን ተመዝግበው ወረፋ እየጠበቁ መሆኑም ከሆስፒታሉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። የዳሌ አጥንት መገጣጠሚያ ህክምና ዋጋ እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ የተነሳ በርካታ አገሮች በጤና መድህን የጥቅም ማዕቀፍ ውስጥ አያካትቱትም።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም