ቀጥታ፡

በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ማህበረሰቡ አብሮነቱን ለማጠናከር ቃል ኪዳን የሚገባበት ቀን ነው - የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች

አዲስ  አበባ  ሀምሌ 18/2011 የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ቀን ማህበረሰቡ አብሮነቱን ለማጠናከር ቃል ኪዳን የሚገባበት እንዲሆን ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን የኪነጥበብ ባለሙያዎች ገለጹ ። የኪነጥበብ ባለሙያዎች ተሳትፎ አስተባባሪ የሆነው አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ ለኢዜአ እንደገለጸው፤ በመጪው ሰኞ በሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ቀን የችግኝ ተከላ ላይ ከ300 በላይ አርቲስቶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። የአረንጓዴአሻራቀንችግኝየሚተከልበትብቻሳይሆንየአንድነትምልክት፣ኢትዮጵያለአፍሪካአርአያየምትሆንበትናበአለምስሟየሚጠራበትታላቅቀንእንደሚሆንምተናግሯል። አርቲስት ቴዎድሮስ እንደተናገረው፤ በዕለቱ በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አንድነታቸውን ለማጠናከር ቃል ኪዳን የሚገቡበት ቀን ይሆናል። የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በባህርዳር፣ ሐዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ ጅማና አዲስ አበባ በመገኘት የችግኝ ተከላ ስራውን የማስተባበርና ቃልኪዳን የማስገባት ስራዎችን እንደሚያከናውኑ ገልጿል። እንደ አርቲስት ቴዎድሮስ ገለጻ፤ ዕለቱ ለኢትዮጵያውያን የሚበጀው ትብብር መሆኑንና በአንድነት የጎላ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ማሳያ ይሆናል። በአሁኑወቅትየአረንጓዴአሻራመርሃግብሩንበተመለከተበማህበራዊሚዲያዎችላይየሚጻፉ አሉታዊነገሮችንሕብረተሰቡከመቀበልእንዲታቀብምመልዕክቱንአስተላልፏል። አርቲስት ቴዎድሮስ እንደገለጸው፤ ችግኝ መትከል የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን የተሻለች አገርን ለትውልድ የማስረከብና ንጹህ አየር የመተንፈስ ጉዳይ ነው። በመሆኑም ማህበረሰቡ ከፖለቲካ አጀንዳ ነጻ ሆኖ አሻራውን ማኖር እንደሚገባውና ለቀጣዩ ትውልድ የሚተላለፈው የሚያኮራ ታሪክ አካል ሊሆን እንደሚገባም መክሯል። በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 200 ሚሊዮን ችግኝ የሚተከል ሲሆን በአገር አቀፍ ደረጃ በተያዘው የክረምት ወቅት ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ደግሞ 4 ቢሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉ ይጠበቃል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም