ቀጥታ፡

17ኛው ዙር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ''ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ’’ የውጭ ምንዛሬ ማበረታቻ እጣ ወጣ

አዲስ አበባ ኢዜአ ሀምሌ 16/2011---17ኛው ዙር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ‘’የይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ’’ የውጭ ምንዛሬ ማበረታቻ አሸናፊ ለሆኑ እድለኞች ዕጣ ወጣ፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢድ አል ፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ከግንቦት 12 እስከ ሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ ባሉ ቀናቶች ያዘጋጀው የውጭ ምንዛሬማበረታቻ እጣ ወጥቷል። አራት ሽልማቶችን ያካተተው ይህ እጣ ዛሬ በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ ወጥቷል። ሽልማቱም በአንደኛ እጣ አንድ አውቶሞቢል መኪና፣ ሁለተኛ እጣ ሁለት ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ፣ ሶስተኛ እጣ 16 የውሃ ማጣሪያና አራተኛ እጣ 64 የስማርት ስልክ እጣዎች ናቸወ። በዚህም በአንደኛ እጣ የቤት አውቶሞቢል አሸናፊ ቁጥር 7460867 ሆኖ ወጥቷል። እንዲሁም ሁለቱ ባለ ሶስት እግር ተሸከርካሪ እጣ አሸናፊዎች ቁጥሮች ደግሞ 7512202 እና 7420277 ናቸው። በሶስተኛና አራተኛ ሽልማት ደግሞ 16 የውሃ ማጣሪያና 64 የስማርት ስልክ ቀፎ አሸናፊዎች እጣው ወጥቶላቸዋል። ባንኩ በቅርብ ጊዜ አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ 18ኛው ዙር ’’የይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ’’ዝግጅቱን አጠናቆ ስራውን እንደሚጀምር ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም